የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ ለ2905 ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጎላቸዉ እንዲለቀቁ ወስኗል። በአማራ ክልል የ598 ተጠርጣሪዎች ክስ ተቋረጠ፡፡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በወሰነው መሰረት በአማራ ክልል ክሳቸው የተቋረጠው ፣ በድምሩ 598 ክስ ሂደታቸው እንዲቋረጥ መደረጉን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቋል፡፡የግለሰቦቹ ጉዳይ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ክሳቸው እንዲቋረጥ ከተደረገ በኋላ የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ ማህበረሰቡ እንደሚቀላቀሉም ተገልጿል፡፡ በዚህም፡-በሰሜን ጐንደር ዞን 224, አዊ ብሔረሰብ 176, ምዕራብ ጐጃም ዞን 1ዐ7, ምስራቅጐጃም ዞን 41, ደቡቡ ወሎ ዞን 17, የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን 14, ደቡቡ ጐንደር ዞን 13, ሰሜን ወሎ ዞን 3, ዋግህምራ ብሔረሰብ ዞን 2 ሰሜን ሸዋ ዞን 1 ክሳቸው መቋረጡ ተገልጿ:: የወልቃይት ኮሚቴ አባላት ኮ/ል ደመቀ ዘውዴን ጨምሮ በይቅርታ ስለመካተታቸው የታወቀ ነገር የለም::
The post Amhara Regional Goverment pardons 2905 prisoners appeared first on Bawza NewsPaper.