Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Water hyacinth and other weeds which threatened lake Tana: BBC

$
0
0

ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው ወንዴ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የውሃ ሳይንስ መምህር እና ተመራማሪ ናቸው። በጣና ዙሪያ መወለዳቸውን የሚገልጹት ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው ላለፉት 15 ዓመታትም በጣና ሐይቅ ላይ በግላቸውም ሆነ ከተማሪዎቻቸው ጋር የተለያዩ ምርምሮችን አድርገዋል።

ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በሐይቁ ዙሪያ ከመሥራታቸውም በላይ በጣና ውሃ ብክለት፣ የአካባቢው የውሃ አዘል መሬቶች፣ የጣና የውሃ ውስጥ ብዝሃ-ህይወት በአጠቃላይ በጣና ደህንነት ዙሪያ የተለያዩ ምርምሮችን አካሂደዋል።

“ሐይቁ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ፈተናዎች እየገጠሙት ነው። የአፈር መከላት፣ የደለል ክምችት፣ ተገቢ ያልሆነ የሥነ-ሕይወት አጠቃቀም፤ ልቅ ግጦሽ እና የባህር ሸሽ እርሻ ተጠቃሾች ናቸው። በተለይ ደግሞ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በሰሜናዊ ምሥራቅ የሐይቁ ክፍል የተከሰተው የእምቦጭ አረም ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል” ይላሉ ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው።

እምቦጭ አረም ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለም። በ1965 ዓ.ም በቆቃ ሐይቅ ላይ ተከስቶ እንደነበር ፕሮፌሰሩ ይገልጻሉ።

የአረሙ ዋነኛ መነሻው ደቡብ አሜሪካ ብራዚል ነው። በጣና ሐይቅ ላይ ከመታየቱ በፊት በ2004 ዓ.ም መገጭ በሚባል ወንዝ ላይ ቀድሞ መከሰቱን ተመራማሪው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

እጅግ አደገኛ የሆነው ይህ መጤ አረም ግንዱን እና ፍሬውን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች የሚራባ መሆኑ በፍጥነት እንዲስፋፋ አስችሎታል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከመገጭ ወንዝ ላይ በመነሳት እስከ 100 ኪሎ ሜትር በመጓዝ የጣና ሐይቅ በአረሙ እንዲሸፈን አድርጓል ይላሉ።

ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የአየር ንብረት ለውጥ እና በእምቦጭ አረም ላይ ያለው ዕውቀት አነስተኛ መሆኑን ይገልጻሉ። ከዚህ የከፋው ግን በአካባቢው አርሶ አደሮች እና ብዝሃ-ህይወት ላይ የሚያደርሰው ችግር ነው።

በሐይቁ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ደስታ ብርሃን እንዳሉት አረሙ ሐይቁን እያጠፋው ነው።

“ከብቶቹ ውሃ የሚጠጡበትን፣ ለልብስ ማጠቢያ እና ለተለያዩ ሥራዎች የምንጠቀምበትን ሃይቅ ልናጣው ነው” ይላሉ በቁጭት። “ከብቶችም አረሙን ሲበሉ ጤናኛ አይሆኑም ሥጋቸውም ሆነ ወተታቸው አይጣፍጥም” ሲሉ ይገልጻሉ።

በግብርና ሥራ የሚተዳደሩት አቶ ምትኬ ፈንቴ በበኩላቸው “አረሙ ከብቶቻችን እየገደለ ነው” ብለዋል።

ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው ወንዴ

ከእምቦጭ በተጨማሪ አዞላ እና ኢፖማ የተሰኙ አረሞችም እየተከሰቱ ነው

“ጣና የገዳሙ ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱም ሃብት ነው”
በጀልባ ሥራ የሚተዳደረው አባይነህ ምናለ አረሙ ለጀልባ ጉዞ የማይመች በመሆኑ የቱሪዝም እንቅስቃሴው ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው ይላል። የአሳ ምርትም ቢሆን በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል። “ድሮ ከአንድ ታንኳ 80 አሳ ይያዝ ነበር። አሁን ግን ከ15 አሳ በላይ አይገኝም” ሲል በሥራው ላይ ያለውን ችግር ይገልጻል።

ጣና ሐይቅን የቱሪዝም መስህብ ካደረጉት ነገሮች መካከል ከ20 በላይ ገዳማትን መያዙ ነው። ከገዳማቱ አንዱ በሆነው እንጦስ እየሱስ ገዳም በተገኘንበት ወቅት እማሆይ ወለተማርያምን “ጣና የገዳሙ ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱም ሃብት ነው” ይላሉ።

እማሆይ ወለተማርያም፤ አረሙ አንጦስ እየሱስ ገዳም አካባቢ አለ መባሉ ጭንቀት ፈጥሮባቸዋል። “አረሙ ሐይቁን ሊያደርቅብን ይችላል የሚል ስጋት አድሮብናል” ይላሉ።

“ምን ዓይነት ፈተና መጣብን ብዬ ነው ያዘንኩት” የሚሉት የገዳሙ አገልጋይ አባ ወልደሰንበት፤ የእርሻ ቦታዎችን የሚይዝ ከሆነ ህዝቡ ሊቸገር ይችላል። ይህ ደግሞ የእኛም ችግር ነው ሲሉ ይናገራሉ።

ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው እንደሚሉት የተፈጥሮ ስጦታ ሆነው እምቦጭ በሌላው የተፈጥሮ ሃብት ጣና ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት እምቦጭ በትክክለኛ ቦታው ላይ ባለመገኘቱ ነው። “እጽዋት እንደ እጽዋት የሚቆጠረው በተፈጠረበት ሃገር ሲሆን በዛም እንደ ተፈጥሮ ፀጋም ይቆጠራል። ለምሳሌ ደንገል ለእኛ ተፈጥሮ ስጦታ ነው” ሲሉ ያስረዳሉ።

“መጤ ሁሉ መጥፎ አይደለም” የሚሉት ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው እንደምሳሌ የሚያነሱት በቆሎ እና በርበሬን ነው። እነዚህ መጤ እጽዋት በሌሎች የተፈጥሮ ጸጋዎች ላይ ጉዳት ሳያደርሱ ጥቅም በመስጠት ላይ ናቸው። እምቦጭ ግን ከዚህ በተቃራኒ በውሃ፣ ሥነ-ህይወትና በሌሎች እጽዋት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ይላሉ። Read More

The post Water hyacinth and other weeds which threatened lake Tana: BBC appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles