Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

ፕሬዚዳንት አልበሽር በመላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጁ

$
0
0

 የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በመላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጁ።

ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በትናንትናው ዕለት በመላ ሀገሪቱ ለአንድ ዓመት የሚፀና የአስቸኳጊዜ አዋጅ ማወጃቸውን አስታውቀዋል ።

ከዚህ ባለፈም ካቢኔያቸውንና በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የግዛት አስተዳዳሪዎችን በማንሳት በወታዳራዊ አዛዦች መተካታቸው ነው የተገለፀው።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዋና አላማም በአልበሽር አስተዳድር ላይ በመላ ሀገሪቱ የተቀጣጣለውን ተቃውሞ ለማክሽፍ ነው ተብሏል።

አልበሽር  በሀገሪቱ ቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት በቅርቡ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ህጋዊ መሰረት የሌለውና የሀገሪቱን ሰላም ለማድፍረስ የታቀደ  ሴራ ሲሉ አጣትለውታል ።

ይሁን እንጂ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከማንኛውን የተቃዋሚ ፓርቲ ጋር  በሰለጠነ መንገድ   ለመወያየት ፍቃደኛ መሆናቸውን በአንክሮ ተናግረዋል ።

በተጨማሪም የሀገሪቱ ፓርላማ ፕሬዚዳንት አልበሽር ለ2020 ምርጫ ለመወዳደር የሚያስችላቸውን ህጋዊ መሰረት ለመስጠት የሚያደርጉትን የህገ- መንግስት ማሻሻያ እንዲያራዝሙ ጥሪ አቅርበዋል ።

በሱዳን በቅርቡ በዳቦና ነዳጅ ዋጋ መናር ምክንያት  የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ፕሬዚዳንት አልበሽር ስልጣናቸውን እንዲለቁ እስከመጠየቅ መድረሱ ይታወሳል ።

በዚህ ሂደትም የመንግስት ወታደሮች በተቃዋሚዎች ላይ ሰላም ለማስከበር በወሰዱት እርምጃ ከ60 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ህይዎት ማለፉን መረጃዎች ያመላክታሉ።
(ኤ.ፍ ቢ.ሲ)


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles