ከለገዳዲ ግድብ ወደ አዲስ አበባ ውሃ ከሚያስተላልፉት ሁለት መስመሮች መካከል አንዱ በድንገት በመሰበሩ የተወሰኑ የመዲናዋ አካባቢዎች ውሃ ተቋርጦባቸዋል።
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው፥ ከሁለቱ የውሃ መስመሮች መካከል ድንገተኛ ስብራት ያጋጠመው ባለ 900 ሚሊ ሊትር የሆነ መስመር ሲሆን፥ አሁን ላይ መስመሩን በመዝጋት ጥገና እየተከናወነ ይገኛል።
በዚሀም ምክንያት በአያት፣ ሰሚት፣ መገናኛ፣ ኮተቤ፣ ሃያ ሁለት፣ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ቦሌ ሚካኤል፣ ካዛንቺስ እና ኡራኤል አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ እንዲሁም፥ 4 ኪሎ፣ 6 ኪሎ፣ ፒያሳ፣ ጥቁር አንበሳ እና ተክለሃይማኖት አካባቢዎች በከፊል እስከ ማክሰኞ ድረስ ውሃ ይቋረጥባቸዋል ብሏል ባለሰልጣኑ።
በመሆኑም ህብረተሰቡ ጥገናው ተጠናቆ መስመሩ ወደ መደበኛ ስርጭት እስከሚገባ ድረስ በትእግስት እንዲጠባበቅ ነው የጠየቀው።
(ኤፍ.ቢ.ሲ)