የኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን የሚገኘውንና የፌዴራል መንግሥት ተቋም የሆነውን የቂንጢቻ ታንታለም ማዕድን ማምረቻ መዝጋቱ በክልሉና በፌዴራል መንግሥት መካከል ውዝግብ ፈጠረ፡፡
የማዕድን ማምረቻው እንዲዘጋ የተወሰነው በአካባቢውና በማኅበረሰቡ ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው በሚል ምክንያት ቢሆንም፣ ዋና ምክንያቱ ግን የማዕድንይዞታውን ለአካባቢው ወጣቶች ተሰጥቷቸው ራሳቸው አምርተው በመሸጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ታስቦ መሆኑን ከሁለቱም ወገኖች መረጃዎች ያመለክታሉ።
የማዕድን፣ ነዳጅና ባዮፊዩል ኮርፖሬሽን ላለፋት 28 ዓመታት ማዕድኑን በማምረት ለውጭ ገበያ ሲቀርብ የነበረ ሲሆን፣ ማዕድኑን እዚሁ በማቀነባበርና እሴት በመጨመር ከፍተኛ የው ምንዛሪ እንዲያስገኝ የፌዴራል መንግሥት መወሰኑ ይታወቃል። በውሳኔው መሠረትም ኮርፖሬሽኑን የሚቆጣጠረው የመንግሥትልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር የቂንጢቻ ታንታለም ማምረቻን በከፊል ለመሸጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ አውጥቶ ነበር፡፡ ሆኖም በክልሉና በኮርፖሬሽኑ መካከልየተፈጠረው ውዝግብ ይህ ጨረታ በወጣበት ወቅት ነው፡፡
ኮርፖሬሽኑ ለአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በየዓመቱ ሦስት ሚሊዮን ብር በጀት እንደሚመድብ ያቀረበው የአማራጭ ሐሳብም በዞኑ አስተዳደርተቀባይነት አላገኘም። ይህንን አጣብቂኝ ሁኔታ ለመፍታትና የቂንጢቻ ታንታለም ማዕድን ማምረቻን ለውጭ አልሚዎች በከፊል ለማዘዋወር የወጣው ጨረታናየተጀመረው ጥረት እንዳይስተጓጎል ለማድረግ የኮርፖሬሽኑ ተቆጣጣሪ የሆነው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር አቶ ግርማ አመንቴ የሚመራ ኮሚቴየኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳን ለማነጋገር መወሰኑን ያገኘናቸው መረጃዎች አመልክተዋል።
source: Reporter
The post Controversy Between the Oromia regional government and the Federal Government against Tantalum production in Guji zone appeared first on Bawza NewsPaper.