Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trump proposes 1.8 million citizenship to undocumented people

$
0
0

የትራምፕ አስተዳደር ሁለት ሚሊዮን ለሚጠጉ በሃገሪቱ ለሚገኙ ሰነድ ለሌላቸው ስደተኞች የአሜሪካ ዜግነትን ለመስጠት እቅድ አዘጋጀ። ለእነዚህ ሰዎች ዋይት ሀውስ ዜግነት የሚሰጠው በአወዛጋቢው የሜክሲኮ ድንበር ላይ አጥር ግንባታ በጀት የሚመደብ ከሆነ በምላሹ ነው።

ከፍተኛ የትራምፕ አማካሪዎች እዚህ ወሳኔ ላይ የደረሱት ከዲሞክራቶች ጋር ድርድር በሚያደርጉበት ዋዜማ ነው። ስለዚህም በመደራደሪያነት የሚያቀርቡት ለስደተኞቹ ዜግነት መስጠትን ሲሆን የግንባታ በጀት ደግሞ ከድርድሩ ማትረፍ የሚፈልጉት ይሆናል።

ይህ መደራደሪያቸው ሰኞ ይፋ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን ለድንበር አጥር ግንባታው የሚጠይቁት በጀት 25 ቢሊዮን ዶላር ነው።

ሜክሲኮ ድንበር ላይ አጥር መገንባትን የሚቃወሙ ዲሞክራቶች አጠቃላይ እቅዱን ተቃውመዋል።

ስለዚህ እቅድ የተሰማው የዋይት ሃውስ ፖሊሲ ሃላፊ ስቴፈን ሚለርና የሪፐብሊካን አማካሪዎች ትናንት ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ቃለ ምልልስ ባደረጉበት ወቅት ነበር።

ሚለር ይህን የዋይት ሃውስ ፕላን አስገራሚም ብለውታል። እቅዱ 1.8 ሚሊዮን ስደተኞች ከ10-12 ዓመት ጊዜ ውስጥ ዜግነት የሚያገኙበትን ደረጃ ያስቀምጣል።

ቁጥሩ ትራምፕ ‘ድሪመርስ’ የሚሏቸው ህፃናት ሳሉ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ የገቡ፤ ነገር ግን በኦባማ አስተዳደር ዘመን በጊዜያዊነት አገሪቱ ላይ እንዲማሩና እንዲሰሩ የተፈቀደላቸውን ሰባት መቶ ሺህ ስደተኞችን ይጨምራል።

ሌሎቹ 1.1 ሚሊዮን የሚሆኑት በተመሳሳይ መልኩ ወደ አገሪቱ የገቡ ነገር ግን በኦባማ አስተዳደር ከለላ ለማግኘት ሳያመለክቱ የቀሩ ናቸው።

በስደተኞች ጉዳይ የሪፐብሊካኖች አክራሪ ድምፅ የሆኑት የምክር ቤት አባል ቶም ኮተን የትራምፕን እቅድ ለጋስና ሰብዓዊነትን የተከተለ ብለውታል።

በተቃራኒው ዲሞክራቶች በእቅዱ ብዙም ደስተኞች አይደሉም። ይልቁንም እነዚህ ስደተኞች ትራምፕ ቤተሰብን ለመነጣጠል በሚከፍቱት ጦርነት መያዣ መሆን አይገባቸውም እያሉ ነው።

ሜክሲኮ ድንበር ላይ ግንብ ለመገንባት የሚወጣው በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የታክስ ከፋዮችን ገንዘብ የሚያባከን ነው እያሉ ነው።

The post Trump proposes 1.8 million citizenship to undocumented people appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles