HELP ~ ኮሜዱያን ልመንህ ታደሰ ይጣራልኮሜዲያን አለባቸው ተካ – ኮሜዲያን እንግዳዘር ነጋ በፈጣሪ ተጠርተው ወዲያ ኛው ዓለም ሄደዋል።የእነርሱ ወዳጅ – የኢትዮጵያ ወርቃማ ልጅ ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ በአዲስ አበባ ጎዳና እጁን እያወዛወዘ እየተንከላወሰ ነው።ልመንህ ከከፍታው ማማ ወርዶ – በአዲስ አበባ ጎዳና … የሚለውን መልዕክት ሰምተው ዝም አሉ?!ልምንህ ታደሰን የሚታደግ ኢትዮጵያዊ ጠፋ?!እረ የሰው ያለህ -ይህንን መልእክት ሼር በማድረግ ለአገር እና ለሕዝብ አድርሱ።***በቶሮንቶ ካናዳ የሚኖረው እና ለሥራ ወደ ኢትዮጽያ የመጣው ኤፍሬም ደስታ በላይነህ መልዕክት ለኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ የሳቃችን ምንጭ ቀልድ አዋቂ የሥዕል ጥበበኛ ለማገዝ የመልካም ሀሳብ አመንጪ የሆነው ወንድማችን ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን ሲሆን ከወንድማችን ኮሜዲያን ደረጀ ኃይሌ ጋርና ከኤፍሬም ደስታ በላይነህ ጋር በመመካከር ይህንን የጎህ ፈንድሚ አካውንት ኤፍሬም እንዲከፍተው አድርገዋል:: ኤፍሬም በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ሥራ ውስጥ የተወዳጁን አለባቸው ተካ (አለቤ ሾውና በተለያዩ የቴሌቪዥንና የዶክመንተሪ ፊልሞች በካሜራና በኤዲተርነት ሲያገለግል የኖረ የጥበብ ቤተሰብ ነው:: ደጋግ የሆናችሁ የሀገሬ ህዝቦች ለእዚህ ተወዳጅ ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ የምታደርጉትን ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን::በሀገር ውስጥ ለሚደረግለት ድጋፍ የኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ አድናቂዎችና ወዳጆች የሀገራችንን ደጋግ ልቦች ድጋፍ ለመቀበል በሀገር ውስጥ በስሙ የሚከፈተውን አካውንት ቁጥር በነገው ዕለት ለጌጡ ተመስገን የፌስቡክ ቤተሰቦች የምናሳውቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።ሊንኩን ተጭነው ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰን ይደግፉ:: https://www.gofundme.com/f/nza7g?utm_source=whatsapp&utm_medium=chat&utm_campaign=p_cf
↧