እንግዶቻችን እንኳን በደህና ወደ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መጣችሁ!!
የኢትዮጵያ ሙዚቃ የጀርባ አጥንት የሆኑት የግጥምና ዜማ ደራሲያን አበበ ብርሃኔ እና ተስፉ ብርሃኔ (ኢንጅነር ባንጃው) በደራሲ አበረ አዳሙ መሪነት በኪነ ጥበብ ዘርፍ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ለመስራት ዛሬ ደብረማርቆስ ገብተዋል።
የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ካውንስለ የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃግብር በማዘጋጀት አቀባበል ያደረገላቸው ሲሆን የቤተሰብነት እውቅናም ሰጥቷቸዋል።
በባህል፣በስነጽሁፍና ቋንቋ ልማት የልህቀት ማዕከል ላይ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይም ሞክክር ተደርጓል።