ታዋቂው የብላክ ፓንተር ፊልም አክተር ቻድዊክ ቦስማን በካንሰር ህመም ከዚህ ዓለም ተለየ።በብላክ ፓንተር ፊልም ዝናን ያተረፈው አሜሪካዊው ቻድዊክ ቦስማን በ43 ዓመቱ ህይወቱ ማለፉን ሮይተርስ ዘግቧል።ላለፉት አራት ዓመታት በአንጀት ካንሰር ህክምናውን ሲከታተል የነበረው ቦስማን ዛሬ ሌሊት ሎስ አንጀለስ በመኖሪያ ቤቱ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።ቦስማን መቼቱን ምስራቅ አፍሪካ ባደረገው እና በመላው ዓለም ተወዳጅ የሆነው ብላክ ፓንተር ፊልም ላይ በመሪ ተዋናይነት ተውኖ የበርካታ ሽልማቶች ባለቤት ነበር።
↧