Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

አብን ከጎንደር ነዋሪዎች ጋር

$
0
0

 የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር እየመከረ ነው።

በምክክሩ የአማራ ሕዝብ ጨቋኝ እንደሆነ ሲነገር መቆየቱና አማራ በሁሉም ዘርፍ ተወካይ እንዳይኖረው መደረጉ ተመላክቷል። ‹‹የነበረው ሥርዓት ፀረ አማራ ነው፤ ይህን ያመጣውም የብሔርተኝነት ፖለቲካ መጣመም ነው›› የሚሉ ሐሳቦችም ተነስተዋል።

የአማራ ብሔርተኝነት መመሥርት የአማራን ጥቅምና ኅልውናው አስጠብቆ ከሌሌች ብሔረሰቦች ጋር በእኩልነት የመኖር ሐሳብ እንደሆነም ነው በምክሩ የተገለጸው።

‹‹አብን ብሔርን መሠረት አድርጎ የተነሳ ቢሆንም ሌሎችን የሚጎዳ፣ የሚውጥ፣ የሚያስገብር ሳይሆን መነሻውን እኩልነት በማድርግ በእኩል ለመኖር የሚያልም ነው። ሌሎችን ብሔረሰቦች የመግፋት ዓላማ የለውም። ይህ ዓይነት መርህ አዋጭም አይደለም›› ያሉት የንቅናቄው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መልካሙ ሹምዬ ናቸው።

አቶ መልካሙ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የንቅናቄው መሰሶ እንደሆነና መዝረፍና መቀማት አስፈላጊ ባለመሆኑ በፍትሐዊ መንገድ ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚሠራም ተናግረዋል። ‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሕዝቦችን በጠላትነት አንፈርጅም፤ ጠላት ሕዝብ የለንም እህት ወንድም ነው ያለን። አብን ፍትሕ፣ ዴሞክራሲ እና እኩልነት መገለጫ መንገዶቹ ናቸው›› ነው ያሉት።

የአማራ ብሔርተኝነት በጎጥ ሳይከፋፈል፣ ከኢትዮጵያዊነት ሳያፈነግጥ፣ ለፍትሕ እና ለእኩልነት የሚሠራ መሆኑንም አቶ መልካሙ ተናግረዋል። የፌዴራሊዝም ሥርዓቱ ተስተካክሎ ሁሉንም ብሔረሰቦች እኩል ተጠቃሚ እንዲያደረግ መሠራት እንዳለበትም ነው ያሳሰቡት። ሁሉም ሕዝብ የሚሳተፍበት ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት መጽደቅ እንደሚገባውም ነው የተናገሩት፡፡

‹‹አብን ለአማራ ሕዝብ ብቻ የቆመ ፓርቲ አይደለም። የትኛውም ዜጋ ፍትሕ ሲጓደልበት የሚጠይቅ እና የሚሠራ ነው›› ብለዋል አቶ መልካሙ በምክክር መድረኩ ባደረጉት ንግግር።
/አብመድ/


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles