የሰላምና ልማት ማህበር 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ የሰላም ሲምፖዚየም አካሄደ፡፡
‘’እርቅና ዘላቂ ሰላም ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች’’ በሚል መሪ ቃል ነው የሰላም ሲምፖዚየሙ የተካሄደው፡፡
በሲምፖዚየሙ ክፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የተፎካካሪ ፓለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና ምሁራን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በዚህ ወቅት ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አልማዝ መኮንን ማህበሩ ለሰላምና ልማት ያደረጋቸውን አስተዋፅዎች አጠናክሮ እንዲቀጥልና በቀጣይም በኢትዮጵያ እና በአካባቢው ሰላም መስፈን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
ተፎካካሪ ፓርቲዎች ልዩነቶቻቸውን በሰላምና በመከባበር ማስኬድ እንዳለባቸው ጠቅሰው የሰላም እሴቶቻችን በማጠናከር ሀገራዊ አንድነት መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የማህበሩ መስራች አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳህቅ በበኩላቸው ማህበሩ ላለፉት 30 ዓመታት ለሰላምና ለልማት እውን መሆን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
ፕሮፌሰሩ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች መካከል ጦርነትን በማስወገድ ወንድማማችነትን መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ለዚህም ግጭት መከላከል እና ማስቀረት የሚያስችሉ ሀገራዊ እሴቶችን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት፡፡
ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ በማስታረቅ ለሰላም እውን መሆን እያንዳንዱ ዜጋ ሀላፊነት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች የሰላም መንገድን ብቻ በመከተል ግጭትን የማራቅ ሀላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
The post ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች የሰላም መንገድን ብቻ በመከተል ግጭትን የማራቅ ሀላፊነት አለባቸው – ፕ/ር ኤፍሬም appeared first on Bawza NewsPaper.