ኢትዮ ቴሌኮም ቅዳሜ ታኅሳስ 13 ቀን 2011 ዓ.ም. ለሪፖርተር በላከው መግለጫ በአዲስ አበባና በጅማ ዞን በቴሌኮም ማጭበርበር ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎች ከነመሣሪያዎቻቸው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታወቀ፡፡
ከተለያዩ የፌዴራልና የክልል ፀጥታ አካላት ጋር በጋራ በተደረገ ክትትል በአዲስ አበባ 34፣ በጅማ ዞን ደግሞ 32 ሲም ቦክሶች መገኘታቸውንም ጠቁሟል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በተለያዩ ጊዜያት በቴሌኮም ማጭበርበር ምክንያት በርካታ ገንዘብ እንደሚያጣ ማስታወቁ የሚታወስ ሲሆን፣ በተለይም ከዓለም አቀፍ ጥሪዎች የሚያገኘው ገቢ በእጅጉ እንደቀነሰበት ሲያስታውቅ ቆይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት፣ ዓርብ ታኅሳስ 12 ቀን 2011 ዓ.ም. የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬ ሕይወት ታምሩ በሰጡት መግለጫ በሕገወጦች ላይ ዕርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀው ነበር፡፡
The post በቴሌኮም ማጭበርበር የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ appeared first on Bawza NewsPaper.