Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታደሰ ቀና አመንቴ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያስተላለፉት መልዕክት

$
0
0

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታደሰ ቀና አመንቴ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያስተላለፉት መልዕክት።

“አጠገባችሁ ያለው ተማሪ ወንድማችሁ እንደናንተው ከምስኪን ቤተሰብ የተገኘ፣ ጭራሮ ለቅማ፣ ጠላ ሽጣ፣ ግፋ ቢል በጉሊት ችርቻሮ ወይም በመንግሥት ስራ ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ የምትኖር የአንተንው እናት የምትመስል እናት/ ሀርሜ አለችው።

እንዳንተው በእርሻ፣ በመለስተኛ ንግድ ወይም በመንግሥት ስራ የሚተዳደር አባት፣ እንዳንተው ነገ ተመርቀህ ለራስህና ለኔ ተሳልፍልኛለህ ብሎ ተስፋ ያሚጥልበትና የሚያዝንለት ወገን ያለው ወገንህ ነዉ። እናም ማንም ከየትም ሆኖ በሚፈጥርልህ በዉል እንኳን ተለይቶ በማይታወቅ ምክንያት ብለህ አታጥቃው። እመነኝ በዩኒቨርሲቲ ዉስጥ ትርፍአልባ ግጭት ደም ገብረህ፣ ወንድምህን ገድለህ በፀፀት አለንጋ እየተገረፍህ እድሜህን ትማቅቃለህ። አሊያም ራስህ ሰለባ ሆናህ የራስህንና የወገንህን ህልም ታጨልማለህ።

ባይሆንስ ምንም ውስጥ ከሌለበት ወንድምህ ተባልተህ ትርፉ ምንድነው? ይሉቁንስ በዚህ የማይደገመውን የካምፓስ ህይወት አጋጣሚ በጋራ በመሆን ለሀገራችሁ ችግር መፍትሔ ፈልጉ። እመነኝ አንድ ሆነህ ከቆምህ ከፊትህ ብሩህ ተስፋ አለ”

By: 

 

The post የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታደሰ ቀና አመንቴ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያስተላለፉት መልዕክት appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles