Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all 1835 articles
Browse latest View live

የእኛ ስሜት እና የቴዲ አፍሮ ቁስል ~አንድ እርምጃ ወደኋላ ሁለት እርምጃ ወደፊት! (ጌታቸው ሺፈራው)

$
0
0

የእኛ ስሜት እና የቴዲ አፍሮ ቁስል

~አንድ እርምጃ ወደኋላ ሁለት እርምጃ ወደፊት!

(ጌታቸው ሺፈራው)

ቴዲ አፍሮ ባህርዳር ላይ “ጃ ያስተሰረያል!”ን ዝፈንልን ተብሎ ሳይዘፍን ከመድረክ ወረደ፣ ሕዝብም ቅር ተሰኘ አሉ። ይህን ስሰማ በሁለቱም ጫማ ውስጥ ገብቼ አየሁት። የኮንሰርት ተሳታፊ እና ዘፋኙን ሆኜ!

ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁስሉ እየጠዘጠዘው ነው። ቴዲ የብሶቱን እንዲዘፍንለት ይፈልጋል። ባህር ዳር ደም ያልደረቀባት ከተማ ነች፣ ቁስሉ ያልጠገገ፣ በየጊዜው እየደማ ያለ ሕዝብ ነው። ትናንት እንኳ ሕዝን የወልዲያን ሰቆቃ ሰምቶ ነው ወደ ኮንሰርቱ የገባው። ሕዝብ የፍቅር ሳይሆን የትግል ዜማ፣ የብሶት ዜማ ነበር መስማት የሚፈልገው።

በሌላ በኩል ደግሞ ቴዲ አፍሮ “ይህን ከዘፈንክ አይቻልም” እየተባለ ፍዳውን አይቷል። ገንዘብ ከስሯል። ዋናው ገንዘቡ አይደለም። አድናቂዎቹን ማግኘት አልቻለም። ሌላው ቀርቶ ስለ መተባበር፣ ስለ ሕዝብ ፍቅር በአካል ተገኝቶ መስበክ አልቻለም! ከ “ጃ” አንፃር ካላየነው በስተቀር አብዛኛው የቴዲ ዘፈን ፖለቲካ ነው። ሀገር የመሰረቱትን እንደሰይጣን የሚጠሉ ገዥዎች ባሉበት ሀገር “ጥቁር ሰው”ን ያህል ፖለቲካ ያለ አይመስለኝም። ቴዲ በቅርቡ ያወጣው አልበም የተወደደው “ጃ ያስተሰራልን”ስላካተተበት አይደለም። ዝም ብሎ ዘፈን ስለሆነም አይደለም። ፖለቲካም ስለሆነ ነው። ተወዳጁ ቴዎድሮስ ካሳሁን ስለዘፈነውም ጭምር ነው!

በመከራ ያለ ሕዝብ ስሜት ለማንም ሊያስቸግር ይችላል። የባሰው ሕዝብ በስልት፣ ቀስ እያልክ ከምትነግረው አፍርጠህለት ግንባርክን ብትባል “ወንድ” ይልሃል። እውነቱን ተናግሮ ከመሸበት ማደር የሚለውም ይህንኑ ነው። ይህ የሕዝብ ስሜት ከበደል ብዛት የመጣ ነው። የብሶት ነው!

ግን በእየ ግላችን እንኳ የምንቀንሳት፣ እንሰንብት፣ ውጭ እንቆይ “ኧረ እነዚህ ሰዎችኮ” የምንልበት አጋጣሚ በርካታ ነው። ገብስ ገብሱን የምናወራበት ብዙ ነው። የምንወደውንም “አታክረው፣ ምን ነክቶህ ነው?፣ ተው እነዚህ ሰዎች!፣ ተው ሞኝ አትሁን፣ አንዳንዴ ብልጠት ያስገልጋል……” እያልን ይደርሳል ከሚባለው ችግር ማይል ርቀን የምንፈራ ብዙ ነን። አንድን ትልቅ ጉዳይ ለማስፈፀም ከዋናው ያነሱ ነገሮችን የምንቀንስበት ጊዜ ብዙ ነው።”ልጆቼን ላሳድግ ብየ እንጅ፣ ትምህርቴን ብጨርስ ኖሮ፣ ውጭ ሀገር ብሆን……” የምንል ሞልተናል። ይህ ሁሉ የሰው ባዶ ፍራት አይደለም። የገዥዎቹ አረመኔነት ነው። እንዲያውም አዲስ የሚሆነው አለመፍራት ነው!

ሰለሞን ተካ ነገ የቴዲን “ጃ ያስተሰረያልን” ቢዘፍን “ይቅር” የሚለው ሰው ያለ አይመስለኝም። ቴዲ ሌላ ሙዚቀኛ ቢዘፍነው ላይሰማ የማይችል ዘፈን ሲዘፍን እንኳ የሚሰማው ሕዝብ “የእኔ ነው!” ስላለው ነው። የ”እኔ ነው” የምትለውን ደግሞ የፈለከውን ሁሉ ስላላደረገልህ አይንህን ለአፈር ልትለው አይገሻም። እንዲያውም የሚወደው አካል የጠየቀውን ያልፈፀመው ምን የከበደ ነገር ገጥሞት ይሆን ብለን መጠየቅ የጥሩ ወዳጅ ባህሪ ነው።

ቴዲ ቋሚ ስራው ዘፈን ነው። ሁሌም ስለዘፈን፣ ስለ ደጋፊዎቹ ነው የሚያስበው። ትናንት ባህርዳር ስቴዲዬም የተገኘው ሕዝብ ደግሞ በአብዛኛው ዘፈንን በተወሰነ የመዝናኛ ጊዜ ብቻ የሚያስታውሰው ነው። ቴዲን ለስንት አንዴ ቢሰማው ነው። ከዘፋኞች ሁሉ ሊያስቀድመው ቢችልም ቴዲ አድማጮን የሚያስበውን ያህል ቴዲን አያስበውም። ቴዲ ለታዳሚው ከዘፋኞች መካከል አንዱ ነው። ዋነኛው ቢሆንም። ለቴዲ ግን ብቸኛው አድማጩ ሕዝብ ነው። ትናንት “ዝፈንልን” ብሎ ለምኖ ሳይሆን ሲቀር ቅር ካለው ሕዝብ በላይ፣ እየተለመነ መዝፈን ያልቻለው ቴዲ ቅሬታ የባሰ እንደሚሆን መገመት ይቻላል።

ቴዲን የሚወደደው የሕዝብ ስሜትን ስለተረዳ ነው። ግን ጃ ያስተሰረያልን ዘፍኖ ቁጭ ቢል አሁን ያገኘውን የሕዝብ ፍቅር ማግኘት ባልቻለ ነበር። በተደጋጋሚ የሕዝብን ስሜት የሚገልፁ ዜማዎች በማውጣቱ ብቻ ሳይሆን ለሕዝብ የከፈለው ዋጋም ይበልጥ ተወዳጅና ታማኝ አድርጎታል። በዚህ ሁሉ ጊዜ ቴዲ ብቻ የሚያውቃቸው ለሕዝብ ያልተገለፁ በደሎች ደርሰውበት ይሆናል። እሱ የበገነበትን፣ የተቆጨበትን፣ ምን አልባት ያለቀሰበትን ሁሉ አልተጋራነውም ይሆናል። እሱ ግን የሕዝብን ስሜት በአደባባይ ገልፆአል። ዛሬ አንድ ዘፈኑን ለመዝፈን ሲከበድ ጭንቀቱን ልንጋራው ይገባል። የምር ስንወደው ቢጨንቀው እንጅ በእኛ አይጨክንም ነበር ማለት ነበረብን። የምንወደው ሰው ለእኛ ስሜት ግዴታ እንዳለበት ሁሉ እኛው ለውሳኔው ቦታ ልንተውለት፣ ለእሱ ስሜትም ግዴታ ሊኖርብን የግድ ነው!

እንደኔ ቴዲ አድናቂዎችን ማግኘት ይፈልጋል። ይህን ሲያደርግ የተደራደረው ነገር “ጃ ያስተሰረያልን” አለመዝፈን ነው። ይህ ለእሱ ልብ የሚሰብር ሊሆን ይችላል። ግን ደግሞ ያለው አንድ ዘፈን ብቻ አይደለም። በሌሎቹ ዜማዎች አድናቂዎቹን እያገኘ፣ አሳካለሁ የሚለውን ለመተግበር ያቀደ ይመስለኛል። ቀስ በቀስ……እንዲሉ። ከአማራ ቲቪ ጋር ከነበረው ቆይታ መረዳት እንዳሚቻለው ስለ ሕዝብ ፍቅር፣ ታሪክ……መስበክ ይፈልጋል። የተወሰነውን አጥቶ ካጣው የተሻለ ነገር ማድረግ ይፈልጋል። ፖለቲከኞቹ ሁለት እርምጃ ወደፊት አንድ እርምጃ ወደኋላ እንደሚሉት ማለት ነው። አንድ እርምጃ ያተርፋል ማለት ነው! ትርፍና ኪሳራ አስልቶ ማለት ነው። ጃ ያስተሰረያልን ብቻ ከስሮ የምኒልክን ታሪክ፣ የቴዎድሮስን ታሪክ፣ የሙስሊም ክርስትያኑን ታሪክ………መስበክ ፈልጓል።

እኔ በበኩሌ ይህ መንገድ አዋጭ ይመስለኛል። እኛ የለመድነው ወደፊት ገፍተን ቁም ስንባል “ቁም ተብያለሁ፣ አይታችኋል” ብለን እማኝ ቆጥረን መቆም ነው። አሊያም ይህ ካልሆነ ፈቀቅ አልልም ብለን ባለበት መርገጥ ወይጭራሽ ቀኝ ኋላ ዙር ነው።

ከምንም በላይ ግን ቴዲ ዘፈነ፣ ንዋይ አዜመ፣ እኛ የራሳችን ጥቅምና ጉዳት ምን ሊሆን ይችላል፣ ምን ሊሆንስ ይገባል ብለን አንቆጥርም። ከፍ ለማድረግ አንጥርም። ያ በሆነበትም ግን ሕዝብ ስሜቱን ገልፆአል። ከፍ ለማድረግ ብንጥር ደግሞ ከዚህ የተሻለ ሊሆን በቻለ ነበር። ቴዲን ከመጠበቅ ከራሳችን የሚጠበቀውንም ማድረግ እንችል ነበር።

ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ከኮንሰርቱ ባህርዳር ምን ልታገኝ እንደምትችል እያወራን ነበር። ብዙዎቻችን በረባ ባረባው ስብሰባ፣ ኮንፈረንስ፣… እየተባለ የት የት እንደሚደረግ እንኳ መረጃው ላይኖረን ይችላል። በምሽት ዜና ዘገባዎች የሚታዩ ስብሰባዎች የት ከተማ፣ የት ሆቴል እንደሚደረጉ እንኳ አስበነው አናውቅም። በቴዲ ኮንሰርት የባህርዳር ባጃጆች፣ ሆቴሎች፣ ታክሲዎች፣ ማተሚያ ቤቶች፣ ጌጣጌጥ የሚሸጡ ወጣቶች የሚያገኙትን መንግስት በአንድ ቀን ቀርቶ በወር በደጀት አይመድብላቸውም።

ከቴዲና ከጃ ያስተሰረያልስ ማን ይበልጣል? የወደድነው በዚህ ዘፈን ብቻ ነው? ከወደድነው ሊዘፍን ያልቻለበት ምክንያትስ ለምን አላስጨነቀንም? ጃ ከእኛ እና ከቴዲ ከማን ይቀርባል? ከፈጣሪው ቴዲ እና ከአድማጮቹ የጃ ያስተሰረያል መከልከል ማንን ያመዋል?

 

The post የእኛ ስሜት እና የቴዲ አፍሮ ቁስል ~አንድ እርምጃ ወደኋላ ሁለት እርምጃ ወደፊት! (ጌታቸው ሺፈራው) appeared first on Bawza NewsPaper.


Fire erupts at Washington DC around little Ethiopia (9th street, NW)

$
0
0

በዛሪው እለት 01/22/2018 ከቀኑ 2፡30 pm በዋሽንግተን ዲሲ በሊትል ኢትዮጽያ (9 ኛ ጎዳና) በተከሰተ የእሳት አደጋ  በሳሊኒ ላውንጅ እና ባር ላይ የንብረት አደጋ ተከስቷል፡፡  በዋሽንግተን ዲሲ የእሳት አደጋ ሰራተኞችም ባደረጉት እርብርብ አደጋው ወደ ለሎች ቤቶች እንዳይዛመት ከፍተኛ አስተዋፆ አድርገደዋል፡፡ የባውዛ ኢትዮጽያ ጋዜጣ እና የ ኢትዮጽያ የሎው ፔጅ  ዋና መስሪያ ቤት እንዲሁመ በርካታ የኢትዮጽያውያን የንግድ ድርጅቶች  በዚሁ አካባቢ እንደመገኘቱ የደረሰው አደጋ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረ ቢሆንም አደጋው በቁጥጥር ስር ውሏል::  በሳሊኒ ላውንጅ እና ባር ላይ በደረሰው የንብረት አደጋ የተሰማንን ሀዘን እንገልፃለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ቪድዮውን ይመልከቱ

D.C LITTLE ETHIOPIA FIRE AT "SALINA RESTAURANT"1936 9TH ST NW, Washington, DC.. "በዋሽንግተን ዲሲ በዘጠነኛዉ ጎዳና የእሳት ቃጠሎ ተነሳ"

D.C LITTLE ETHIOPIA FIRE AT "SALINA RESTAURANT"1936 9TH ST NW, Washington, DC.."በዋሽንግተን ዲሲ በዘጠነኛዉ ጎዳና የእሳት ቃጠሎ ተነሳ"

Posted by Bawza Ethiopian Newspaper on Monday, January 22, 2018

D.C LITTLE ETHIOPIA FIRE AT "SALINA RESTAURANT"1936 9TH ST NW, Washington, DC.. "በዋሽንግተን ዲሲ በዘጠነኛዉ ጎዳና የእሳት ቃጠሎ ተነሳ"

D.C LITTLE ETHIOPIA FIRE AT "SALINA RESTAURANT"1936 9TH ST NW, Washington, DC.."በዋሽንግተን ዲሲ በዘጠነኛዉ ጎዳና የእሳት ቃጠሎ ተነሳ"…Share and Like us……www.bawza.com

Posted by Bawza Ethiopian Newspaper on Monday, January 22, 2018

The post Fire erupts at Washington DC around little Ethiopia (9th street, NW) appeared first on Bawza NewsPaper.

Teddy Afro new message after Bahirdar concert

$
0
0

ከአራት አመታት በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያው የሆነው የሙዚቃ ድግሴ እጅግ ባመረ መልኩ ተጠናቋል ። የባህርዳር ህዝብ ወደ ከተማዋ ስገባ ካደረገልኝ አቀባበል ጀምሮ በነበረኝ ቆይታ ባሳዩኝ ፍቅርና ክብር እንዲሁም በተደረገልኝ መስተንግዶ ልቤ ተነክቷል- እወዳችዋለሁ ! የዝግጅቱ ዕለት ስቴዲየም ተገኝታችሁ የታደማችሁ በሙሉ በተለይም ደግሞ ከሩቅ አካባቢዎች ከአራቱም ማዕዘን መጥታችሁ ዝግጅቱን ለተካፈላችሁ ሁሉ ምስጋናዬና ፍቅሬ ከልብ ነው ።

የሙዚቃ ስራዎቼን ማቅረብ ከጀመርኩ ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የማይገባኝን ሁሉ እንዳደረገልኝ በድጋሚ በመመስከር ሁሌም በፍፁም ታማኝነት እናንተን እንደማገለግል ሳረጋግጥ በታላቅ ኩራት ነው ።

እግዜር ያክብርልኝ !

አመሰግናለሁ ባህር ዳር !
አመሰግናለሁ ኢትዮጵያ

The post Teddy Afro new message after Bahirdar concert appeared first on Bawza NewsPaper.

UN High Commissioner for Human Rights Press briefing on Woldia massacre, Ethiopia

$
0
0

We are extremely concerned by the use of force by security officials against worshippers celebrating the Ethiopian Orthodox festival of Epiphany this weekend that left at least seven people dead and a number injured.

The incident, in Woldiya City in Amhara Regional State on 20 January, reportedly took place when the security forces tried to stop people from chanting anti-government songs and allegedly opened fire on them. Protesters reportedly later blocked roads and destroyed a number of properties.

This incident is all the more regrettable, as it comes just two weeks after Ethiopia’s ruling coalition, the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front, officially announced its intention to undertake reforms.

We call on the authorities to ensure that the security forces take all feasible measures to prevent the use of force.

We understand that the President of Amhara Regional State, who confirmed that there had been deaths and injuries, said there would be what he termed a “careful examination” of the incident.

We urge for this to be a prompt, independent, impartial and effective investigation to ensure those responsible for any violations are held accountable. We also call on the Government to undertake the necessary legal and policy reforms, along with guidance and training, to create the conditions for law enforcement officials to operate in line with international standards.

The post UN High Commissioner for Human Rights Press briefing on Woldia massacre, Ethiopia appeared first on Bawza NewsPaper.

A book about the life story of the legendary musician Ali Bira is to be released

$
0
0

#Ethiopia- A book about the life story of the legendary musician Ali Bira is to be released soon. It is written both in Afaan #Oromo, #Amharic & English. According to the author of the book, Dr. Surafel Gelgelo of the Addis Abeba University History Department, it took three years to complete the production.

The book is the first comprehensive production about the life story of artist Ali Bira and it involved his full participation from the beginning to the end. Artist Ali Bira himself gave hist approval of the book’s accuracy during a presser briefing.
Please see full video of the news below.

#Ethiopia- A book about the life story of the legendary musician Ali Bira is to be released soon. It is written both in Afaan #Oromo, #Amharic & English. According to the author of the book, Dr. Surafel Gelgelo of the Addis Abeba University History Department, it took three years to complete the production. The book is the first comprehensive production about the life story of artist Ali Bira and it involved his full participation from the beginning to the end. Artist Ali Bira himself gave hist approval of the book's accuracy during a presser held this morning, according to Dire Tube.Please see full video of the news below.

Posted by Addis Standard on Tuesday, January 23, 2018

The post A book about the life story of the legendary musician Ali Bira is to be released appeared first on Bawza NewsPaper.

Interview with Artist Surafel Shiferaw “ሊጋባው በየነ” ማነው? VOA

$
0
0

“እንደኮራ ሔደ እንደተጀነነ
ጠጅ ጠጣ ሲሉት ውሃ እየለመነ
ሊጋባው በየነ”

“ሊጋባው በየነ” ማነው

ሊጋባው በየነ

“እንደኮራ ሔደ እንደተጀነነጠጅ ጠጣ ሲሉት ውሃ እየለመነሊጋባው በየነ”“ሊጋባው በየነ” ማነው የሚል ጥያቄን አንስቶ ሱራፌል ሽፈራው ( @djphatsu )ድምፃዊው ግዛቸው ተክለማርያም አነጋግሯል።#GabinaVOA #VOAAmharic #EthiopianMusic #Ethiopianmusic2018 #djphatsu

Posted by VOA Amharic on Tuesday, January 23, 2018

The post Interview with Artist Surafel Shiferaw “ሊጋባው በየነ” ማነው? VOA appeared first on Bawza NewsPaper.

What REALLY happens to your body when you don’t get enough sleep

$
0
0

While one restless night’s sleep is unlikely to cause health problems in the long term, consecutive nights of poor sleep can do more harm than many people realise.

And if this is you you’re not alone, with a health survey by the Australian Sleep Health Foundation finding that 33 to 45 per cent of adults sleep either poorly or not long enough most nights.

‘Scientists are now uncovering the strong relationship between our gut microbiome and sleep,’ the Supercharged Food founder said.

‘When our circadian rhythms are disrupted, the bacteria of our gut can be negatively affected. The line of connection between the gut and the brain, known as the “gut brain axis” becomes compromised, a little bit like when you play broken telephone.’
Read more:

The post What REALLY happens to your body when you don’t get enough sleep appeared first on Bawza NewsPaper.

ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል? (ዳንኤል ክብረት)

$
0
0

የጸጥታ ኃይሎች በወልድያ ነዋሪዎች ላይ የፈጸሙት ግድያ በምንም ዓይነቱ መመዘኛ ከውግዘት የሚያመልጥ አይደለም፡፡ በአንድ በኩል ‹ጸረ መንግሥት ዝማሬ ያሰሙ ነበር›፣ በሌላ በኩል ደግሞ ‹ድንጋይ ይወረውሩ ነበር› የሚሉት ምክንያቶች የጸጥታ ኃይሎች በሕዝብ ላይ ጥይት እንዲተኩሱ የሚያበቁ ሕጋዊና ሞራላዊ ምክንያቶች አይደሉም፡፡ ማንኛውም ጸጥታን የማስከበር ሥራ መከናወን ያለበት ሰላምን በሚያሰፍን፣ የሰዎችን ሕይወትና ንብረት በሚጠብቅና ተመጣጣኝ የሆነ ኃይልን ለመጠቀም በሚፈቅድ ሁኔታ መሆን አለበት፡፡
በኃይል የሚፈታ ችግር እንደሌለ መንግሥት ራሱ ከማናችንም በላይ የሚያውቀው ነገር ነው፡፡ የዛሬውን መንግሥት የመሠረተው ኢሕአዴግ ወደ በረሓ እንዲገባ ያደረገው ደርግ ችግሮችን ሁሉ በውይይት ሳይሆን በኃይልና በኃይል ብቻ ለመፍታት በመፈለጉ መሆኑን በየግንቦት ሃያ በዓሉ ስንሰማው ኖረናል፡፡ ለሰው የሚጠላውን ኃጢአት ራሱ ከመሥራት በላይ ውድቀት የለም፡፡ በዓሉ የአንድ ቀን በዓል ነው፡፡ ቢታገሡት ያልፍ ነበር፡፡ ሌላ ችግር ይከሰታል ተብሎ ከተጠረጠረና መረጃ ከተሰበሰበ እንኳን አያሌ የችግር መፍቻ አማራጮች ነበሩ፡፡ ‹የጸጥታ ችግርም› ‹የጸጥታ ኃይሎች›ም እኛ ሀገር ብቻ አይደለም ያሉት፡፡ ባለ ሥልጣኖቻችንም ለልምድ ልውውጥ በየሀገሩ ሲሄዱ ነው የሚኖሩት፡፡ ምነው ታድያ የተሻለ አማራጭ መማር አቃታቸው?
በዓሉ ሕጻናት፣ አረጋውያን፣ ዐቅመ ደካሞች፣ ነፍሰ ጡሮች፣ አካል ጉዳተኞች ሳይቀሩ የሚታደሙበት በዓል ነው፡፡ እንዴት ነው ወደነዚህ ሁሉ የሚተኮሰው? እንዴትስ ነው ‹ችግር ፈጠሩ› የተባሉትን አካላት ከሌሎች ለመለየት የሚቻለው? ጥይቱስ እንዴት ነው ከ9 ዓመት ሕጻን የሚጀምረው? እንዲህ ባሉ ዓመታዊ በዓላት ቀን የሚፈጠር ግፍ ከልጅ ልጅ ለመታወስና የበቀልን ስሜት ለመቀስቀስ ቀላል መሆኑን እንዴት ለማሰብ ከበደን? ከዚህ በኋላ ወልድያ ላይ የቃና ዘገሊላ በዓል ቃና ዘገሊላ ብቻ ሆኖ የሚታሰብ ይመስለናን? ገና ይዘፈንበታል፣ ይፎከርበታል፣ ይተረትበታል፣ ሙሾ ይወረድበታል፣ ውሎ ለቅሶ ይዋልበታል፡፡ ለመሆኑስ በየልቅሶ ቤቱ የተቀመጠው ሕዝብ ስለ ልማትና ዴሞክራሲ፣ ስለ መንገድና ትምህርት ቤት፣ ስለ ባቡርና አውሮፕላን ማረፊያ የሚጨዋወት ይመስለናል? ገና ተዝካር፣ መት ዓመት፣ ሰባት ዓመት፣ ሃያ አንድ ዓመት የሙታን በዓል አለ፡፡ በነዚህ ዘመናት ሁሉ ምን የሚባል ይመስላችኋል?
እንዲህ ላሉ ችግሮችስ ጥይት መፍትሔ አለመሆኑን ባለፉት ሁለት ዓመታት ሀገሪቱ ያለፈችበት ሁኔታ ብቻ እንዴት አያስተምረንም? ይልቅ ለምን የችግሩን ምንጭ ለማድረቅ አንሠራም? ‹የሚያስለቅስ ነገር ነግሮ አታልቅስ ይለኛል› የሚል የትግርኛ አባባል አለ፡፡ ሕዝቡ ለምን ባሰው? ወጣቶቹ ለምን ተቃወሙ? የዚህ ሁሉ ችግር ምንጩስ ምንድን ነው? ብሎ መሥራት አይሻልም፡፡ ለምን ሕዝብን ከሕዝብ ወገንን ከወገን የሚያጋጭና ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ቂም እንዲቋጠር ይፈለጋል? ለምንስ የዘርና የጎሳ መልክ እንዲይዝ ይፈለጋል? ወንጀለኞችስ ለምንድን ነው በጎሳ ካባ ውስጥ እንዲደበቁ ሁኔታዎች የሚመቻቹት? ከመሬት መንቀጥቀጡ(shock) በላይ ድኅረ መንቀጥቀጡ(aftershock) ውጤቱ የከፋ መሆኑን አናውቅምን? ችግሩንስ ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል?
አሁንም ባለ ሥልጣኖቻችን ቆም ብለው የማሰቢያ ጊዜያቸው ባያሳጥሩት መልካም ነው፡፡ ችግርን ከመፍታት ይልቅ ‹የከተማዋ ሁኔታ እየተረጋጋ ነው› ዓይነት ዜና ራስን ማታለያ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ስብሰባ ደምን አድርቆ አያውቅም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዝምታ በመቀበል፣ ፋታም በፍጻሜነት ሊተረጎም አይችልም፡፡ በበላይ ዘለቀ ምክንያት በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ወታደሮች ግፍ የተፈጸመበት የጎጃም ገበሬ ምነው ዝም አለ? ሲባል
ዝም አልክ ይለኛል ዝምታ የታለ
ውስጤ እየጮኸ ነው እየተቃጠለ
ብሎ የገጠመው የልቅሶ ግጥም ሁኔታውን በሚገባ የሚገልጠው ይመስለኛል፡፡ አሁንም ሰይፍ ወደ ሰገባው፣ ቃታም ወደ ቦታው፣ ይግባ፡፡ ወንጀለኞችም ወደ ፍርድ፣ ችግሮችም ወደ መሠረታዊ መፍትሔ ይምጡ፡፡ መንግስትም ወደ ልቡናው ይመለስ፡፡

The post ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል? (ዳንኤል ክብረት) appeared first on Bawza NewsPaper.


”ወንድሜን በአምስት ጥይት በሳስተው ነው የገደሉት” BBC

$
0
0

በወልዲያ ከተማ በጥምቀት በዓል ማግስት የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ በርካቶች ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወቃል።

መንግሥት የሟቾች ቁጥር ሰባት ነው ቢልም ያነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ግን የሟቾችን እና የቁስለኞችን ቁጥር ከፍ ያደርጉታል።

ከከተማዋ ነዋሪዎች እንደሰማነው ከሟቾቹ መካከል አዛውንቶች እና እድሚያቸው በአስራዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኙ ሁለት ታዳጊዎች ይገኙበታል።

ከዚህ በተጨማሪ በጥምቀት በዓል ማግስት ከተገደሉት መካከል በወልዲያ ከተማ በብረታ ብረት ሥራው የሚታወቀው ገብረመስቀል ጌታቸው ይገኝበታል።

ገብረመስቀል እድሜው ወደ 35 የሚጠጋ ሲሆን ባለትዳር እና የ5 ዓመት ሴት ልጅ አባት ነበር።

ገብረመስቀልን በቅርብ የሚያውቁት ጠንካራ ሰራተኛ ስለመሆኑ ይመስክሩለታል። ብረመስቀል የብረታ ብረት ድርጅት የነበረው ሲሆን በወልዲያ ከተማም የንግድ ህንጻ እየገነባ ነበር።

ገብረመስቀል በተገደለበት ቀን እና አሁን ቤተሰቡ ስለሚገኘበት ሁኔታ ወንድሙን ኪዳኔ ጌታቸውን አነጋግረነው ነበር።

ገብረመስቀል ጥር 12 የሚካኤል ታቦትን ሽኘቶ ሲመለስ መብራት ኃይል የሚባል ቦታ ላይ በጸጥታ ኃይሎች በተተኮሱ ጥይቶች እንደተገደለ ከቤተሰቡ ሰምተናል። ወንድሙ ኪዳኔ ”ወንድሜን አምስት ቦታ ነው በሳስተው የገደሉት። እንዳይተርፍ ነው 5 ጊዜ በጥይት የመቱት” ሲል በምሬት ይናገራል።

ኪዳኔ ዕለቱን ሲያስታውስ ”ግርግር እንደተነሳ ደጋግሜ ስልክ ደወልኩለት፤ አያነሳም። ብጠብቀውም መልሶ አይደውልም። በጣም ስለተጨነኩኝ ወደ ሆስፒታል ልፈልገው ሄድኩኝ።

”አንገቱ ላይ፣ ደረቱ ላይ፣ ሆዱ ላይ እና ብልቱ ላይ አምስት ጊዜ በጥይት የተመታ እና በደም የተሸፈነውን የወንድሜን አስከሬን ሆስፒታል ውስጥ አገኘሁ” ይላል ሁኔታውን ሲያስታውስ።

”ማመን ነው ያቀተኝ። ወንድሜ ላይ ግፍ ነው የተፈጸመው። ገብረመስቀል አንድ ጥይት የሚበቃው ልጅ ነበር። የቤተሰቡን አንጀት ነው የቆረጡት። እናቱን ወዳጅ፤ አባቱን አክባሪ ነበር። እሱን ብቻ ሳይሆን ቤተሰቡን ነው የገደሉት። የአምስት ዓመት ሴት ልጅ አለችው አሁን የተፈጠረውን ነገር መቀበል አልቻለችም” ሲል ኪዳኔ በቁጭት ይናገራል።

 

Read more:

The post ”ወንድሜን በአምስት ጥይት በሳስተው ነው የገደሉት” BBC appeared first on Bawza NewsPaper.

Drunk man tries to walk up the street |ሞቅታ መጨረሻው! በመጠጥ ደስታ ይገኛል ብላችሁ መጠን አትለፉ እንዲህ ትሆናላችሁ!

The secrete of Ethiopian book of Enoch

$
0
0

 

ሁሉም ኢትየዮጵያዊ ሊያየው የሚገባ የመፅሐፈ ሄነኖክ ሚስጥር ምንድነው? ለምንምዕራባውያን ከኢትዮጵያ መፅሐፋን ለመውሰድ ፈለጉ?ኢሉምናቲ በመፅሐፈ ሄኖክ እይታ ክፍል አንድ ……….. ለሁሉም እንዲዳረስ ሼር ማድረጉን ኮሜንት መስጠቱን አትርሱ

ሁሉም ኢትየዮጵያዊ ሊያየው የሚገባ የመፅሐፈ ሄነኖክ ሚስጥር ምንድነው? ለምንምዕራባውያን ከኢትዮጵያ መፅሐፋን ለመውሰድ ፈለጉ?ኢሉምናቲ በመፅሐፈ ሄኖክ እይታ ክፍል አንድ ……….. ለሁሉም እንዲዳረስ ሼር ማድረጉን ኮሜንት መስጠቱን አትርሱ

Posted by Ethiopia orthodox Nat ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ናት on Tuesday, August 15, 2017

The post The secrete of Ethiopian book of Enoch appeared first on Bawza NewsPaper.

Deaths reported in Kobo town Northern Amhara region of Ethiopia

$
0
0

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የቆቦ ከተማ ቀበሌ 01 ነዋሪ፤ ከትናንት ጀምሮ በነበረው ግጭት አንድ ታዳጊን ጨምሮ በርካቶች መገደላቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የሟቾችን ቁጥር በተመለከተ ያገኘናቸው መረጃዎች የተለያዩ ሲሆኑ ከሆስፒታል ምንጮች ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

እንደ ነዋሪዎች ከሆነ ግን ቢያንስ ሶስት እና ከዚያ በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በጸጥታ ኃይል አባላት ላይም ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ጨምረው ተናግረዋል።

ያነጋገርናቸው ሌላኛው የቆቦ ነዋሪ የግጭቱን መነሻ ሲያስረዱ፤ ”በወልዲያ ከተማ የተፈጸመው ግድያ ቆቦ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረትን ፈጥሮ ነበር። ይህ በእንዲህ እያለ ንብረታችን ሊዘረፍ ወይም ሊወድምብን ይችላል ብለው የሰጉ ሰዎች ንግድ ቤቶቻቸውን በመዝጋት ንብረት ለማሸሽ ሞክረው ነበር። አንዳንድ ወጣቶችም ‘እዚህ ምንም ሳይፈጠር እንዴት ይህን ታደርጋላችሁ’ ብለው መጠየቃቸውን ተከትሎ ግርግር ተፈጠረ ከዚያም ወደ ግጭት አመራ” ሲሉ ያስረዳሉ።

በከተማዋ ተቃውሞ የተጀመረው ትናንት ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ እንደነበር እና ተቃውሞው ወደ ግጭት ተሸጋግሮ የንግድ ቤቶችን እና የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን ማቃጠል የተጀመረው ግን 10 ሰዓት አካባቢ መሆኑን ከከተማዋ ነዋሪዎች መረዳት ችለናል።

ዛሬ ሐሙስ እሰከ ጠዋቱ 3 ሰዓት ድረስ ከተማዋ ምንም እንኳን ውጥረት ውስጥ ብትቆይም ግጭት አልነበረም የሚሉት ሌላው ነዋሪ ”ከ3 ሰዓት በኋላ ግን በርካታ ወጣቶች ዘለቀ እርሻ ልማት ወደሚባል ድርጅት በመሄድ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ ትራክተሮችንና የእርሻ መሳሪያዎችን አወደሙ። ከዚህ በተጨማሪም የድረጅቱ ህንጻ ላይም ጉዳት ደርሷል” ሲሉ ያስረዳሉ።

እንደ ነዋሪዎቹ አባባል የእርሻ ድርጅቱ የጥቃቱ ኢላማ የሆነው ”ከአርሶ አደሩ በርካታ ሄክታር መሬት ተነጥቆ ለዘለቀ እርሻ ልማት ድርጅት ተሰጥቷል የሚል ቅሬታ በመኖሩ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ከዘለቀ እርሻ ልማት ድርጅት በተጨማሪ ኪወ የእርሻ ልማት እና ባለቤትነቱ የሆላንዳውያን የሆነ ሌላ የእርሻ ልማት ድርጅቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የኪወ እርሻ ልማት ባለቤት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የመንግሥት ተቋማትም የጥቃቱ ኢላማዎች ነበሩ። ትናንት ፍርድ ቤት ተቃጥሎ እንደነበር ያስታወሱት ነዋሪ ዛሬ ደግሞ የትምህርት ጽ/ቤት፣ የብአዴን ጽ/ቤት እና የመንግሥት ደጋፊ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች ቤት እና የንግድ ተቋማት ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ንብረታቸው የተቃጠለባቸው ግለሰቦች የመንግሥት ደጋፊዎች ብቻ ናቸው ያሉ ነዋሪዎች ቢኖሩም፤ ብሄራቸውን መሰረት በማድረግ የንግድ ተቋማቸው ላይ ጥቃት የተፈጸመባቸው እንዳሉም የሚናገሩ አሉ።

ከነዋሪዎቹ መረዳት እንደቻልነው አሁን በከተማዋ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጸጥታ ኃይል አባላት ወደ ከተማዋ በመግባታቸው አንጻራዊ የሆነ መረጋጋት ተፈጥሯል።

በጉዳዩ ላይ መረጃ እንዲሰጡን የክልሉን የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት፣ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም አስተዳደር እና ጸጥታ ጉዳዮችን በስልክ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ከወልዲያ በቅርብ እርቀት ላይ በምትገኘው ሮቢት ከተማም ግጭት እንዳለ ተሰምቷል።

The post Deaths reported in Kobo town Northern Amhara region of Ethiopia appeared first on Bawza NewsPaper.

Interview with a new Artist Nazret Hailemariam: VOA

$
0
0

በውጭ ሀገር እየኖሩ ሙዚቃ መስራት ይከብዳል
ናዝሬት ኃይለማሪያም ስለ አዲሱ ነጠላ ዜማዋ ‘ናማ”፣ በውጭ እየኖሩ ሙዚቃ የመስራት ፈተናዎችን  ትነግረናለች። ቀጣዩን ቃለ ምልልስ ይከታተሉ::

በውጭ ሀገር እየኖሩ ሙዚቃ መስራት ይከብዳል

በውጭ ሀገር እየኖሩ ሙዚቃ መስራት ይከብዳልየጋቢና እንግዳ ናዝሬት ኃይለማሪያም ስለ አዲሱ ነጠላ ዜማዋ ‘ናማ”፣ በውጭ እየኖሩ ሙዚቃ የመስራት ፈተናዎችን በጋቢና ተሳፍራ ትነግረናለች።#GabinaVOA #VOAAmharic #EthiopianMusic #Ethiopia

Posted by VOA Amharic on Thursday, January 25, 2018

The post Interview with a new Artist Nazret Hailemariam: VOA appeared first on Bawza NewsPaper.

የቆቦ ህዝባዊ ተቃዉሞ፤ ግጭትና ግድያ: DW amharic

$
0
0

ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ ለተቃዉሞ አደባባይ የወጡ የከተማ ነዋሪወች እና የፀጥታ ሀይሎች ተጋጭተዉ ከ አምስት በላይ ሰወች መሞታቸዉ ተገለፀ።ተቃዉሞዉ በወልደያ ከተማ የጥምቀት በዓልን ሊያከብሩ  በወጡ ሰዎች ላይ የተፈፀመዉን ግድያ ለማዉገዝ የተደረገ ነበር።

Read more 

The post የቆቦ ህዝባዊ ተቃዉሞ፤ ግጭትና ግድያ: DW amharic appeared first on Bawza NewsPaper.

የወልድያን_ጭፍጨፋ አስመልክቶ #የኦነግ_መግለጫ

$
0
0

የወያኔ መንግስት የተለያዩ ሃይማኖት ተከታይ የኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የሚያደርሰውን ግድያና ኣሰቃቂ ጉዳት ይበልጥ ኣጠናክሮ መቀጠሉን በወልደያ የጥምቀት በዓልን ለማክበር በተሰባሰቡ ዜጎች ላይ በፈጸመው ወንጀል ኣረጋግጧል። ስርዓቱ የጥምቀት በዓልን ለማክበር የተሰባሰቡ ምዕመናንን “የተቃውሞ ድምጽ ኣሰምታችኋል” በሚል ወንጅሎ፥ እንደልማዱ የታጠቁ ሃይሎቹን ኣሰማርቶ በከፈተው ተኩስ ከ20 በላይ ዜጎች ተገድለው ሌሎች በኣስሮች የሚቆጠሩ ቆስለዋል።

የሕወሃት/ኢህኣዴግ ፋሽስት ቡድን በተለያዩ ጊዜያት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ የፖለቲካ ኣጀንዳውን ለማራመድ ባደረገው ጥረት በዜጎች ላይ ሲያደርስ ከነበረው ጉዳት በተጨማሪ የሃገሪቷ ህዝቦች እንደባህላቸውና እምነታቸው ፈጣሪያቸውን ለማምለክና ለማመስገን በተገናኙበት ቦታ፡ በጦርና የደህንነት ሃይሎቹ ተኩስ ከፍቶ በመቶዎች ሲገድልና ለከፋ ጉዳት ሲዳርግ እንደነበር በሀር-ሰዲ የኢሬቻ በዓል በኦሮሞዎች ላይ የፈጸመው እልቂት የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ለኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ሀር-ሰዲ ላይ በተሰበሰቡት በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ የኦሮሞ ዜጎች ላይ የሽብር ሃይሎቹን ኣሰማርቶባቸው የፈጸመው ኣሰቃቂ የጅምላ ግድያ መቸውም የማይረሳ ጠባሳን የፈጠረ ሲሆን፡ ይህም የወያኔ ስርዓት ለየትኛውም የሃገሪቷ ባህልና ሃይማኖት ክብር እንደሌለው ያረጋግጣል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በወልደያ ለጥምቀት በዓል በተሰበሰቡ የክርስትና እምነት ተከታይ ዜጎች ላይ የተፈጸመው ወንጀል የዜጎችን የሃይማኖት ነጻነት መብት የጣሰና በሁሉም ኣካላት ሊወገዝ የሚገባው እርኩስ ተግባር መሆኑን እየገለጸ፡ ድርጊቱን ኣጥብቆ ያወግዛል። ይህ ኣረመኔያዊ ድርጊት ኣምባገነኑ የወያኔ መንግስት ሲያደርስ ከነበረው ጥፋት ትምህርት ወስዶ ለመታረም ኣለመዘጋጀቱንና ለሁሉም ሃይማኖቶች ጠላት መሆኑን ይበልጥ ያሳየ እርምጃ ነው።
የሃገሪቷ ህዝቦች እያካሄዱት ባለው #የኣንገዛም_ባይነት ተቃውሞ በተለይ ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ እያፋፋመ ባለው የጭቆና ፍጻሜ ኣመጽ ውጥረት ውስጥ የገባው ወያኔ፡ በሌላ በኩል የሶማሌ ልዩ ሃይል በሚላቸው የሽብር ቡድኖቹ ኣማካይነት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ዘመቻ ኣጠናክሮ በመቀጠል ላይ ይገኛል። ይህም ስርዓቱ በሃገሪቷ ውስጥ #ሽብርና_ቀውስ ኣስፋፍቶ ግድያና ሰቆቃ በመፈጸም እራሱን ከውድቀት በመታደግ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ያለውን እቅድ የሚያሳይ ነው።

ባጠቃላይ ይህን መሰሉ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ ሊገታ የሚችለው የወያኔ/ሕወሃት መንግስት ከስር መሰረቱ ተወግዶ፡ በህዝቦች ሙሉ ፈቃድ ላይ በተመሰረተ ስርዓትና በህዝቡ በተመረጠ መንግስት ሲተካ ብቻ መሆኑን #ኦነግ ያሳስባል። ይህንን እውን ለማድረግም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ተጨቋኝ ህዝቦች እጅ ለእጅ ተያይዘው፥ በህዝቦች እልቂት ኑሮውን እያደላደለ ያለውን ስርዓት ከላያቸው ላይ ለማንሳት እያካሄዱት ያለውን ፍልሚያ እንዲያፋፍሙ ኦነግ መልእክቱን ያስተላልፋል።

ዘመኑ የጭቆና ፍጻሜ ዘመን ነው!
ድል ለኦሮሞ ህዝብ!
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
ጥር 22 ቀን 2018ዓም

The post የወልድያን_ጭፍጨፋ አስመልክቶ #የኦነግ_መግለጫ appeared first on Bawza NewsPaper.


The embattled prime minister, Hailemariam Desalegn, may soon resign: The economist

$
0
0

LIFE in Maekelawi, a prison in Addis Ababa, the capital of Ethiopia, had a predictable rhythm. Three times a day, Atnaf Berhane and Befekadu Hailu were hauled from the dank, dark cell they nicknamed “Siberia” for three hours of interrogation and beating. Mr Hailu was flogged across his bare feet with an electric cable. Mr Berhane escaped this particular cruelty. “I was lucky,” he says.Read more

The post The embattled prime minister, Hailemariam Desalegn, may soon resign: The economist appeared first on Bawza NewsPaper.

10 Things You should Know About the First World War

$
0
0

#1. A Global Scale War

The war involved 30 nations from 1914- 1918.

#2. War of production

As nations struggled to get enough men and equipment for their armed forces, it turned into a war of production where countries mobilized their natural resources to produce equipment for army including rifles, machine guns, tanks and artillery shells.

#3. Tanks were developed during WWI

The British were the first to develop tanks during the war and it was a top secret work. Even the workers who were assembling the pieces didn’t know what they were. Moreover, they were initially called ‘landships’ but were later changed to ‘tanks’ to confuse the enemy.

#4. Ambulances

Ambulances were being used for the first time.

Read more

The post 10 Things You should Know About the First World War appeared first on Bawza NewsPaper.

Ethiopia: Oromia Regional Government pardons 2345 Political prisoners

$
0
0

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለ2 ሺህ 345 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

ለህግ ታራሚዎቹ ይቅርታ ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ መሆናቸውን የቢሮው ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ገልፀዋል።

ይቅርታ ከተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች መካከልም 1 ሺህ 539 ሰዎች ፍርደኞች የነበሩ ናቸው።

እንዲሁም 557 ሰዎች ደግሞ ምርመራ እየተደረገባቸው የነበሩ ሲሆን፥ 250 ሰዎች ጉዳያቸው በፍርድ ቤት በመታየት ላይ የነበሩ መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል።

የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተሾመ ግርማ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ በመሳተፍ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ናቸው።

አቶ ተሾመ ግርማ፥ የይቅርታው መነሻ በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያሳለፈው ውሳኔ አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

በህይወት ማጥፋት ላይ የተሳተፉ፣ በከባድ አካል ጉዳት ያደረሱና በትላልቅ የመሰረት ልማቶች ላይ ጉዳት ያደረሱት በይቅርታው አልተካተቱም ብለዋል።

በዛሬው እለት ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎችም የተሃድሶ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ እንደሚለቀቁም ሃላፊው አስታውቀዋል።

source: Fanabc.com

The post Ethiopia: Oromia Regional Government pardons 2345 Political prisoners appeared first on Bawza NewsPaper.

Trump proposes 1.8 million citizenship to undocumented people

$
0
0

የትራምፕ አስተዳደር ሁለት ሚሊዮን ለሚጠጉ በሃገሪቱ ለሚገኙ ሰነድ ለሌላቸው ስደተኞች የአሜሪካ ዜግነትን ለመስጠት እቅድ አዘጋጀ። ለእነዚህ ሰዎች ዋይት ሀውስ ዜግነት የሚሰጠው በአወዛጋቢው የሜክሲኮ ድንበር ላይ አጥር ግንባታ በጀት የሚመደብ ከሆነ በምላሹ ነው።

ከፍተኛ የትራምፕ አማካሪዎች እዚህ ወሳኔ ላይ የደረሱት ከዲሞክራቶች ጋር ድርድር በሚያደርጉበት ዋዜማ ነው። ስለዚህም በመደራደሪያነት የሚያቀርቡት ለስደተኞቹ ዜግነት መስጠትን ሲሆን የግንባታ በጀት ደግሞ ከድርድሩ ማትረፍ የሚፈልጉት ይሆናል።

ይህ መደራደሪያቸው ሰኞ ይፋ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን ለድንበር አጥር ግንባታው የሚጠይቁት በጀት 25 ቢሊዮን ዶላር ነው።

ሜክሲኮ ድንበር ላይ አጥር መገንባትን የሚቃወሙ ዲሞክራቶች አጠቃላይ እቅዱን ተቃውመዋል።

ስለዚህ እቅድ የተሰማው የዋይት ሃውስ ፖሊሲ ሃላፊ ስቴፈን ሚለርና የሪፐብሊካን አማካሪዎች ትናንት ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ቃለ ምልልስ ባደረጉበት ወቅት ነበር።

ሚለር ይህን የዋይት ሃውስ ፕላን አስገራሚም ብለውታል። እቅዱ 1.8 ሚሊዮን ስደተኞች ከ10-12 ዓመት ጊዜ ውስጥ ዜግነት የሚያገኙበትን ደረጃ ያስቀምጣል።

ቁጥሩ ትራምፕ ‘ድሪመርስ’ የሚሏቸው ህፃናት ሳሉ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ የገቡ፤ ነገር ግን በኦባማ አስተዳደር ዘመን በጊዜያዊነት አገሪቱ ላይ እንዲማሩና እንዲሰሩ የተፈቀደላቸውን ሰባት መቶ ሺህ ስደተኞችን ይጨምራል።

ሌሎቹ 1.1 ሚሊዮን የሚሆኑት በተመሳሳይ መልኩ ወደ አገሪቱ የገቡ ነገር ግን በኦባማ አስተዳደር ከለላ ለማግኘት ሳያመለክቱ የቀሩ ናቸው።

በስደተኞች ጉዳይ የሪፐብሊካኖች አክራሪ ድምፅ የሆኑት የምክር ቤት አባል ቶም ኮተን የትራምፕን እቅድ ለጋስና ሰብዓዊነትን የተከተለ ብለውታል።

በተቃራኒው ዲሞክራቶች በእቅዱ ብዙም ደስተኞች አይደሉም። ይልቁንም እነዚህ ስደተኞች ትራምፕ ቤተሰብን ለመነጣጠል በሚከፍቱት ጦርነት መያዣ መሆን አይገባቸውም እያሉ ነው።

ሜክሲኮ ድንበር ላይ ግንብ ለመገንባት የሚወጣው በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የታክስ ከፋዮችን ገንዘብ የሚያባከን ነው እያሉ ነው።

The post Trump proposes 1.8 million citizenship to undocumented people appeared first on Bawza NewsPaper.

Controversy Between the Oromia regional government and the Federal Government against Tantalum production in Guji zone

$
0
0

የኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን የሚገኘውንና የፌዴራል መንግሥት ተቋም የሆነውን የቂንጢቻ ታንታለም ማዕድን ማምረቻ መዝጋቱ በክልሉና በፌዴራል መንግሥት መካከል ውዝግብ ፈጠረ፡፡

የማዕድን ማምረቻው እንዲዘጋ የተወሰነው በአካባቢውና በማኅበረሰቡ ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው በሚል ምክንያት ቢሆንም፣ ዋና ምክንያቱ ግን የማዕድንይዞታውን ለአካባቢው ወጣቶች ተሰጥቷቸው ራሳቸው አምርተው በመሸጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ታስቦ መሆኑን ከሁለቱም ወገኖች መረጃዎች ያመለክታሉ።

የማዕድን፣ ነዳጅና ባዮፊዩል ኮርፖሬሽን ላለፋት 28 ዓመታት ማዕድኑን በማምረት ለውጭ ገበያ ሲቀርብ የነበረ ሲሆን፣ ማዕድኑን እዚሁ በማቀነባበርና እሴት በመጨመር ከፍተኛ የው ምንዛሪ እንዲያስገኝ የፌዴራል መንግሥት መወሰኑ ይታወቃል። በውሳኔው መሠረትም ኮርፖሬሽኑን የሚቆጣጠረው የመንግሥትልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር የቂንጢቻ ታንታለም ማምረቻን በከፊል ለመሸጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ አውጥቶ ነበር፡፡ ሆኖም በክልሉና በኮርፖሬሽኑ መካከልየተፈጠረው ውዝግብ ይህ ጨረታ በወጣበት ወቅት ነው፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በየዓመቱ ሦስት ሚሊዮን ብር በጀት እንደሚመድብ ያቀረበው የአማራጭ ሐሳብም በዞኑ አስተዳደርተቀባይነት አላገኘም። ይህንን አጣብቂኝ ሁኔታ ለመፍታትና የቂንጢቻ ታንታለም ማዕድን ማምረቻን ለውጭ አልሚዎች በከፊል ለማዘዋወር የወጣው ጨረታናየተጀመረው ጥረት እንዳይስተጓጎል ለማድረግ የኮርፖሬሽኑ ተቆጣጣሪ የሆነው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር አቶ ግርማ አመንቴ የሚመራ ኮሚቴየኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳን ለማነጋገር መወሰኑን ያገኘናቸው መረጃዎች አመልክተዋል።

source: Reporter

The post Controversy Between the Oromia regional government and the Federal Government against Tantalum production in Guji zone appeared first on Bawza NewsPaper.

Viewing all 1835 articles
Browse latest View live