ተወዳጁ የባህል ሙዚቃ ድምፃዊ አርቲስት ይሁኔ በላይ ለመጭው የኢትዮጵያ የፋሲካ በአል አዲስ ነጠላ ዜማ እንደሚለቅ ከሁለት ቀን በፊት መዘገባችን ይታወሳል።
በአርቲስቱ ፊስቡክ ገጽ ላይ እንዳገኘነው “እስቱዲዬ ነን ያለነው ! እንዳትውል ተክፍተህ” አዲሱ ነጠላ ዜማ እየደረሰ ነው ! አብረውኝ ለሚደክሙት ሙዚቀኞቼ ጭብጨባ ለግሱልኝ! በደንብ እንዲሰሩ:: ስማቸውን እየጠቀሳችሁ!” በማለት የዜናውን ትክክለኛነት ያረጋገጠልን ሲሆን በዛሬው እለት በደረሰን የሲዲ ፍላየርም አብረውት የተሳተፉ የሙዚቃ ባለሙያዎች የሚከተሉት ናቸው።
1.ዜማ ና ግጥም፡ አበበ በርሀኔ
2.ሙዚቃ ቅንብር:ሄኖክ ነጋሽ
3.ሳክስፎን: ተክሉ እሸቴ
4.ክራር: ፋንታሁን አባተ
5.ማሲንቆ: ዳዊት ልሳን
እንዲሁም ልዩ ምስጋና ለአበርሀም ውልዴ አቅርቧል።
አርቲስቱ በቅርብ ስራዎቹ(ሰከን በል እና ጣና በሚሉ ዜማዎቹ)ከፍተኛ ተደማጭነት እንደነበራቸው እናስታውሳናል። ”ሰከን በል’ የተሰኘ ዜማው በ2008 ዓም በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል በነበረ ህዝባዊ አመፅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች አጋርነቱን ለመግለፅ የለቀቀው የቁርጥ ቀን ልጅ መሆኑን እናስታውሳለን።
ከዚህም በተጨማሪ በጣና ሀይቅ ላይ የደረሰውን የእንቦጭ አረም ለመከላከል የሚረዳ ወገኑን ለማስተባበር የሚውል ”ጣና“ የተሰኘ ነጠላ ዜማ በመልቀቅ በድጋሚ አስደምሞናል። እንዲሁም ይህን ዜማውን በተለያዩ የአሚሪካ ከተሞች በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረኮች በመገኝት የወገን እና የሀገር ተቆርቋሪነቱን አሳይቷል።
ለማንኛውም አዲሱን ነጠላ ዜማ “እንዳትውል ተከፍተህ” እንደደረሰን የምናስደምጣችሁ መሆኑን ቃል እንገባለን።
The post Artist Yehunie Belay new single for Ethiopian Easter( እንዳትውል ተከፍተህ….!!): Update appeared first on Bawza NewsPaper.