ተወዳጁ የባህል ሙዚቃ ድምፃዊ አርቲስት ይሁኔ በላይ ለመጭው የኢትዮጵያ የፋሲካ በአል አዲስ ነጠላ ዜማ እንደሚለቅ በትላንትላው እለት መዘገባች ይታወሳል። በዛሪው ዕለት በድምፃዊው የፊስቡክ ገፁ ላይ ዜማውን እንደሚለቅ ማረጋገጫ አግኝተናል። #yehunie belay
አርቲስቱ በቅርብ ስራዎቹ(ሰከን በል እና ጣና በሚሉ ዜማዎቹ)ከፍተኛ ተደማጭነት እንደነበራቸው እናስታውሳናል። ”ሰከን በል’ የተሰኘ ዜማው በ2008 ዓም በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል በነበረ ህዝባዊ አመፅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች አጋርነቱን ለመግለፅ የለቀቀው የቁርጥ ቀን ልጅ መሆኑን እናስታውሳለን።
ከዚህም በተጨማሪ በጣና ሀይቅ ላይ የደረሰውን የእንቦጭ አረም ለመከላከል የሚረዳ ወገኑን ለማስተባበር የሚውል ”ጣና“ የተሰኘ ነጠላ ዜማ በመልቀቅ በድጋሚ አስደምሞናል። እንዲሁም ይህን ዜማውን በተለያዩ የአሚሪካ ከተሞች በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረኮች በመገኝት የወገን እና የሀገር ተቆርቋሪነቱን አሳይቷል።
ለማንኛውም አዲሱን ነጠላ ዜማ “እንዳትውል ተከፍተህ” እንደደረሰን የምናስደምጣችሁ መሆኑን ቃል እንገባለን።
The post Artist Yehunie Belay new single for Ethiopian Easter( እንዳትውል ተከፍተህ….!!) appeared first on Bawza NewsPaper.