Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Bekele Gerba and three others sentenced for six months more in jail for contempt of court

$
0
0

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ተከሳሾች ዛሬ በዋለው ችሎት ተጨማሪ የስድስት ወር እስራት ቅጣት ተጣለባቸው።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ የወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ ስማቸው ሲጠራ ባለመነሳታቸውም ፍርድ ቤቱን አላከበራችሁም በሚል ነው ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው።

ፍርድ ቤቱ ከዚህም በፊት በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች ሶስት ተከሳሾችን ችሎት በመድፈር የስድስት ወር ቅጣት መጣሉ የሚታወስ ነው።

ቅጣቱ የተላለፈው በወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 449/23 መሰረት ችሎቱን በመድፈር በሚል መሆኑንም የአቶ በቀለ ገርባ ጠበቃ አብዱልጅባር ሁሴን ይናገራሉ።

“በድምፅ አቤት አላሉም፤ ቆመውም አላከበሩንም የሚል ካልሆነ በስተቀር መገኘታቸውን እጅ በማውጣት አሳይተዋል” የሚሉት አብዱልጅባር ጨምረውም ” እሳቸውን ወክለን መገኘታቸውንም ጠበቆቻቸው ተናግረናል” ይላሉ።

ከዚህም በፊት ማስረጃዎችንና የመከላከያ ምስክሮችን በሚያቀርቡበት ወት ተከሳሾች አብረዋቸው እንደማይቆሙና እጅ በማውጣት ብቻ መገኘታቸውን የሚያሳዩበት አካሄድ እንደነበርም አቶ አብዱልጅባር ያስረዳሉ።

“ፍርድ ቤቱ ሰበብ ፈልጎ ነው ይህንን ቅጣት የጣለባቸው፤ ችሎት መድፈር ህጉ ውስጥ የተካተተው የፍርድ ቤቱን ስራ የሚያደናቅፍ እንዳይሆን እንዲሁም የፍርድ ቤቱን ክብር የሚያጎድፍ ድርጊት ሲከናወን እንጂ የዳኞችን ግላዊ ክብር ለማስጠበቅ አላስከበራችሁም ብሎ ይህንን ውሳኔ መስጠት የሀገሪቱን የፍትህ ስርዓት የወረደ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ” በማለት አብዱልጅባር ተናግረዋል።

ከተከሳሾቹ አንዱ የሆኑት አዲሱ ቡላላ ቤተሰብ ሀልካሜ ጡራም በበኩሏ “በፍርድ ቤቱ ተስፋ እንደሌላትና በውሳኔውም አዝኛለሁ” ስትል ለቢቢሲ ገልፃለች።

ፍርድ ቤቱ በተጨማሪም ለየካቲት 28 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በክሳቸው ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ መድረስ አለመድረሱን ምንም አይነት ፍንጭ እንዳልሰጠ አቶ አብዱልጅባር በተጨማሪ ገልፀዋል።

The post Bekele Gerba and three others sentenced for six months more in jail for contempt of court appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles