Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

የወልድያን_ጭፍጨፋ አስመልክቶ #የኦነግ_መግለጫ

$
0
0

የወያኔ መንግስት የተለያዩ ሃይማኖት ተከታይ የኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የሚያደርሰውን ግድያና ኣሰቃቂ ጉዳት ይበልጥ ኣጠናክሮ መቀጠሉን በወልደያ የጥምቀት በዓልን ለማክበር በተሰባሰቡ ዜጎች ላይ በፈጸመው ወንጀል ኣረጋግጧል። ስርዓቱ የጥምቀት በዓልን ለማክበር የተሰባሰቡ ምዕመናንን “የተቃውሞ ድምጽ ኣሰምታችኋል” በሚል ወንጅሎ፥ እንደልማዱ የታጠቁ ሃይሎቹን ኣሰማርቶ በከፈተው ተኩስ ከ20 በላይ ዜጎች ተገድለው ሌሎች በኣስሮች የሚቆጠሩ ቆስለዋል።

የሕወሃት/ኢህኣዴግ ፋሽስት ቡድን በተለያዩ ጊዜያት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ የፖለቲካ ኣጀንዳውን ለማራመድ ባደረገው ጥረት በዜጎች ላይ ሲያደርስ ከነበረው ጉዳት በተጨማሪ የሃገሪቷ ህዝቦች እንደባህላቸውና እምነታቸው ፈጣሪያቸውን ለማምለክና ለማመስገን በተገናኙበት ቦታ፡ በጦርና የደህንነት ሃይሎቹ ተኩስ ከፍቶ በመቶዎች ሲገድልና ለከፋ ጉዳት ሲዳርግ እንደነበር በሀር-ሰዲ የኢሬቻ በዓል በኦሮሞዎች ላይ የፈጸመው እልቂት የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ለኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ሀር-ሰዲ ላይ በተሰበሰቡት በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ የኦሮሞ ዜጎች ላይ የሽብር ሃይሎቹን ኣሰማርቶባቸው የፈጸመው ኣሰቃቂ የጅምላ ግድያ መቸውም የማይረሳ ጠባሳን የፈጠረ ሲሆን፡ ይህም የወያኔ ስርዓት ለየትኛውም የሃገሪቷ ባህልና ሃይማኖት ክብር እንደሌለው ያረጋግጣል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በወልደያ ለጥምቀት በዓል በተሰበሰቡ የክርስትና እምነት ተከታይ ዜጎች ላይ የተፈጸመው ወንጀል የዜጎችን የሃይማኖት ነጻነት መብት የጣሰና በሁሉም ኣካላት ሊወገዝ የሚገባው እርኩስ ተግባር መሆኑን እየገለጸ፡ ድርጊቱን ኣጥብቆ ያወግዛል። ይህ ኣረመኔያዊ ድርጊት ኣምባገነኑ የወያኔ መንግስት ሲያደርስ ከነበረው ጥፋት ትምህርት ወስዶ ለመታረም ኣለመዘጋጀቱንና ለሁሉም ሃይማኖቶች ጠላት መሆኑን ይበልጥ ያሳየ እርምጃ ነው።
የሃገሪቷ ህዝቦች እያካሄዱት ባለው #የኣንገዛም_ባይነት ተቃውሞ በተለይ ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ እያፋፋመ ባለው የጭቆና ፍጻሜ ኣመጽ ውጥረት ውስጥ የገባው ወያኔ፡ በሌላ በኩል የሶማሌ ልዩ ሃይል በሚላቸው የሽብር ቡድኖቹ ኣማካይነት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ዘመቻ ኣጠናክሮ በመቀጠል ላይ ይገኛል። ይህም ስርዓቱ በሃገሪቷ ውስጥ #ሽብርና_ቀውስ ኣስፋፍቶ ግድያና ሰቆቃ በመፈጸም እራሱን ከውድቀት በመታደግ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ያለውን እቅድ የሚያሳይ ነው።

ባጠቃላይ ይህን መሰሉ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ ሊገታ የሚችለው የወያኔ/ሕወሃት መንግስት ከስር መሰረቱ ተወግዶ፡ በህዝቦች ሙሉ ፈቃድ ላይ በተመሰረተ ስርዓትና በህዝቡ በተመረጠ መንግስት ሲተካ ብቻ መሆኑን #ኦነግ ያሳስባል። ይህንን እውን ለማድረግም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ተጨቋኝ ህዝቦች እጅ ለእጅ ተያይዘው፥ በህዝቦች እልቂት ኑሮውን እያደላደለ ያለውን ስርዓት ከላያቸው ላይ ለማንሳት እያካሄዱት ያለውን ፍልሚያ እንዲያፋፍሙ ኦነግ መልእክቱን ያስተላልፋል።

ዘመኑ የጭቆና ፍጻሜ ዘመን ነው!
ድል ለኦሮሞ ህዝብ!
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
ጥር 22 ቀን 2018ዓም

The post የወልድያን_ጭፍጨፋ አስመልክቶ #የኦነግ_መግለጫ appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles