Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Deaths reported in Kobo town Northern Amhara region of Ethiopia

$
0
0

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የቆቦ ከተማ ቀበሌ 01 ነዋሪ፤ ከትናንት ጀምሮ በነበረው ግጭት አንድ ታዳጊን ጨምሮ በርካቶች መገደላቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የሟቾችን ቁጥር በተመለከተ ያገኘናቸው መረጃዎች የተለያዩ ሲሆኑ ከሆስፒታል ምንጮች ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

እንደ ነዋሪዎች ከሆነ ግን ቢያንስ ሶስት እና ከዚያ በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በጸጥታ ኃይል አባላት ላይም ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ጨምረው ተናግረዋል።

ያነጋገርናቸው ሌላኛው የቆቦ ነዋሪ የግጭቱን መነሻ ሲያስረዱ፤ ”በወልዲያ ከተማ የተፈጸመው ግድያ ቆቦ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረትን ፈጥሮ ነበር። ይህ በእንዲህ እያለ ንብረታችን ሊዘረፍ ወይም ሊወድምብን ይችላል ብለው የሰጉ ሰዎች ንግድ ቤቶቻቸውን በመዝጋት ንብረት ለማሸሽ ሞክረው ነበር። አንዳንድ ወጣቶችም ‘እዚህ ምንም ሳይፈጠር እንዴት ይህን ታደርጋላችሁ’ ብለው መጠየቃቸውን ተከትሎ ግርግር ተፈጠረ ከዚያም ወደ ግጭት አመራ” ሲሉ ያስረዳሉ።

በከተማዋ ተቃውሞ የተጀመረው ትናንት ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ እንደነበር እና ተቃውሞው ወደ ግጭት ተሸጋግሮ የንግድ ቤቶችን እና የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን ማቃጠል የተጀመረው ግን 10 ሰዓት አካባቢ መሆኑን ከከተማዋ ነዋሪዎች መረዳት ችለናል።

ዛሬ ሐሙስ እሰከ ጠዋቱ 3 ሰዓት ድረስ ከተማዋ ምንም እንኳን ውጥረት ውስጥ ብትቆይም ግጭት አልነበረም የሚሉት ሌላው ነዋሪ ”ከ3 ሰዓት በኋላ ግን በርካታ ወጣቶች ዘለቀ እርሻ ልማት ወደሚባል ድርጅት በመሄድ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ ትራክተሮችንና የእርሻ መሳሪያዎችን አወደሙ። ከዚህ በተጨማሪም የድረጅቱ ህንጻ ላይም ጉዳት ደርሷል” ሲሉ ያስረዳሉ።

እንደ ነዋሪዎቹ አባባል የእርሻ ድርጅቱ የጥቃቱ ኢላማ የሆነው ”ከአርሶ አደሩ በርካታ ሄክታር መሬት ተነጥቆ ለዘለቀ እርሻ ልማት ድርጅት ተሰጥቷል የሚል ቅሬታ በመኖሩ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ከዘለቀ እርሻ ልማት ድርጅት በተጨማሪ ኪወ የእርሻ ልማት እና ባለቤትነቱ የሆላንዳውያን የሆነ ሌላ የእርሻ ልማት ድርጅቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የኪወ እርሻ ልማት ባለቤት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የመንግሥት ተቋማትም የጥቃቱ ኢላማዎች ነበሩ። ትናንት ፍርድ ቤት ተቃጥሎ እንደነበር ያስታወሱት ነዋሪ ዛሬ ደግሞ የትምህርት ጽ/ቤት፣ የብአዴን ጽ/ቤት እና የመንግሥት ደጋፊ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች ቤት እና የንግድ ተቋማት ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ንብረታቸው የተቃጠለባቸው ግለሰቦች የመንግሥት ደጋፊዎች ብቻ ናቸው ያሉ ነዋሪዎች ቢኖሩም፤ ብሄራቸውን መሰረት በማድረግ የንግድ ተቋማቸው ላይ ጥቃት የተፈጸመባቸው እንዳሉም የሚናገሩ አሉ።

ከነዋሪዎቹ መረዳት እንደቻልነው አሁን በከተማዋ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጸጥታ ኃይል አባላት ወደ ከተማዋ በመግባታቸው አንጻራዊ የሆነ መረጋጋት ተፈጥሯል።

በጉዳዩ ላይ መረጃ እንዲሰጡን የክልሉን የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት፣ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም አስተዳደር እና ጸጥታ ጉዳዮችን በስልክ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ከወልዲያ በቅርብ እርቀት ላይ በምትገኘው ሮቢት ከተማም ግጭት እንዳለ ተሰምቷል።

The post Deaths reported in Kobo town Northern Amhara region of Ethiopia appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles