Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Ethiopia: All those arrested due to the protest in Woldia has been released

$
0
0

በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ የቃና ዘገሊላ በዓል ለማክበር በወጡ ሰዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ታስረው የነበሩ ሰዎች ሙሉ በሙሉ መፈታታቸውን የዞኑ የፀጥታ ኃላፊ አቶ አደራው ጸዳሉ ገለጹ፡፡

ታሳሪዎቹ ሊፈቱ የቻሉት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በወልዲያ ተገኝተው ከከተማው ወጣቶች፣ የሐይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ሲያደርጉ ከወጣት ተሳታፊዎች በተነሳ ጥያቄ መሆኑን አቶ አደራው ገልጸዋል፡፡

‹‹ወጣቶች እንዲፈቱ በጠየቁት መሠረት እንዲፈቱ ተደርጓል፤›› ሲሉ የፀጥታ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በስብሰባው ተሳታፊ የነበሩ ወጣቶች በነፃነት ሐሳባቸውን ሲያንሸራሽሩ እንደነበር የገለጹት ኃላፊው፣ ከውይይቱ በኋላ የከተማው ፀጥታ እንደተረጋጋ ገልጸዋል፡፡

በግጭቱ የተጎዱ ሰዎች ትክክለኛ ቁጥርና የደረሰው የንብረት ውድመት መጠን የማጣራት ሂደት ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ አቶ አደራው ተናግረዋል፡፡

ቀን ላይ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አማረ ጎሹ ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ሰባት ሰዎች እንደሞቱና 15 ሰዎችም እንደተጎዱ መናገራቸውን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

The post Ethiopia: All those arrested due to the protest in Woldia has been released appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles