በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ በኪነ-ጥበብ ሥራዎቻቸዉ ለህዝባቸው አስተዋፅዖ ላደረጉና እያደረጉ ያሉ ሰዎችን የሚያበረታታና በሥራዎቻቸዉ እዉቅና የሚሰጥ «ኦዳ አዋርድ» የተሰኘዉ የሽልማት ዝግጅት ጥር 5 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሚገኘው የኦሮሚያ የባህል ማዕከል አዳራሽ ዉስጥ በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።
በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው በተባለዉ በዚህ ዝግጅት ላይ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ አባ ገዳዎች፣ ምሁራኖችና ወጣቶች ታደመዋል። የኦዳ አዋርድ ወይም የሽልማት ሥነ-ስርዓቱ በድራማ፣ በፊልምና በሙዚቃ ኪነ-ጥበብ 15 ምድብ እንደነበረዉ የሽልማቱ መስራችና ጋዜጠኛ በሻቱ ቶለማርያም ተናግራለች። ይሁን እንጅ በሻቱ ከእነዚህ 15 ምድቦች መካከል ሁለቱ ምድብ «ለየት ያለ» መሆኑን ነዉ የገለፀችዉ።
The post የሁለት ዘመን ፈርጦች፦ አሊ ቢራ ፤ ሃጫሉ ሁንዴሳ: «ኦዳ አዋርድ» appeared first on Bawza NewsPaper.