እቺኮ ሌላ ናት፤
ሁሉም እኔ ነኝ ልክ ~አውቃለሁ ሚልባት፣
ብሽሽቅ የሚያሸት~ ብሽቅ የሚያብብባት፣
ስድብ የሚነግስ ~ተንኮል የሚያምርባት፣
እቺኮ ሌላ ናት፤
መለያየት መፍትሄ~ ጠብ ራብ የሆናት፣
ስርቆት የሚከብር~ እውነት የሚያፍርባት፣
ጠብ ከፍቅር ቀሎ~ ነብስ የሚረግፍባት፣
እቺ እገር ሌላ ናት፤
የዘር ችርቻሮ ~ ንግድ የሚጦፍባት፣
አዋቂ እንደ ጭሎ~ የሚጎተትባት
እቺኛዋ ኢትዮጵያ ~ግዴለም ሌላ ናት፣
ያቺኛዋ ኢትዮጵያ ~ እናታችን የት ናት?!፤
እግዚአብሔር ሆይ አንተ መተንፈስን አትከለክል… ስለዚህ በሰጠኸን ነፃነት እንተነፍሳለን….መንግስትህ ትምጣ ፍቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን…. አሜን!!!
Abraham Wolde Balageru
The post እናታችን የት ናት?! | ከእውቁ አብርሃም ወልዴ appeared first on Bawza NewsPaper.