ናፍቆቴ!!
‹‹ደህና ሁኝ ልትለኝ ቆመሃል ከፊቴ?
ቁርጥ መሆኑ ነው
አንተም የመሄድህ እኔም የመቅረቴ፡፡
እንዲህ ከሆነማ!
ስንሰነባበት ከአንገት ከደረትህ
ያፈሰስኩት እንባ፣
አጅቦ ያድርስህ ሀገርህ እስክትገባ፡፡
አንተ የሰው ሀገር ሰው
ከቶ ሳላስብህ ሳላልምህ ደርሰህ፣
የልቤን ስብራት በፍቅርህ ጠግነህ፣
የጨለማ ህይወቴን በብርሃን ተክተህ፡፡
ሆነኸኝ ነበረ ደስታ ፈንጠዝያ፣
የህይወቴን ክፍተት ጎዶሎዬን መሙያ፡፡
ግና….
ታይቶ እንደሚጠፋ የጠዋቷ ፀሃይ
ነው የተፈረደ
ጅምሩ ፍቅራችን እንዲህ ሆኖ እንዳናይ
ማንን እከሳለሁ? ከማ እጋፋለሁ?
ቁርጥ ከሆነማ!
እኔም የመቅረቴ አንተም የመሄድህ፣
‹‹ደህና ሁኝ ስትለኝ››
ያፈሰስኩት እንባ ከአንገት ከደረትህ፣
ሀገርህ እስትገባ አጅቦ ያድርስህ!
አጭር ልቦለድ
በህሊና ተፈራ 1996 ተጻፈ
(እንደጠዋት ጀምበር ብቅ ብሎ የጠፋ የፍቅር
አጋር ለገጠማቸው)
The post ያጀብህ እንባዬ appeared first on Bawza NewsPaper.