Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

$
0
0

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

“…..ይህ የቀኝ አዝማች ምስጋናው የህይወት ታሪክና የቅኔን ስብስብ የያዘ መጽሐፍ የ20ኛውን ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ በተለይም የፖለቲካና የስነ~ቃል ታሪክ ለሚያጠኑ ተመራማሪዎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ የታመነ ነው።
ብዙም ባልተዳሰሰውና በውል ባልተጠናው የስነ~ቃልና የትውፊታዊ ሙዚቃ ታሪክ ላይ ትኩረት ላላቸው ተማሪዎችና ተመራማሪዎች ደግሞ አርአያ ነው።”
“አበባው አያሌው በአ.አ.ዩ.የኢትዮጵያ ስነ ጥበባት ታሪክ መምህርና ተመራማሪ”ስለ መጸሐፉ ከተናገሩት
በሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ የመጻሕፍት ንባብና ውይይት ዝግጅት ክፍል ከኢትዮጲስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር እሁድ ነሐሴ 14,2009 ዓ,ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ “በሁሉም አለበል” በተጻፈና “ታሪክን በቅኔ” በተሰኘ መጽሐፍ ላይ በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ (ወመዘክር) አዳራሽ ውይይት ይካሄዳል።
በእለቱ ለውይይቱ መነሻ የሚያቀርቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፎክሎር የPHD ተማሪ እና “ፎክሎር:ምንነቱና የትኩረት አቅጣጫ” የተሰኘ መጽሐፍ ጸሐፊ የሆኑት አቶ ሰለሞን ተሾመ ናቸው።
ውይይቱን የሚመራልን ደግሞ የታሪክ ባለሞያና የቋንቋ መምህር የሆነው ሰለሞን ተሰማ ጂ,ነው።
ፍላጎት ያለው ሁሉ በፕሮግራሙ እንድትታደሙ ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ በአክብሮት ይጋብዛል።

The post ሁላችሁም ተጋብዛችኋል! appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles