Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

በ2050 ከአለማችን ህዝብ ሩብ ያህሉ አፍሪካውያን ይሆናሉ ተባለ

$
0
0

የአፍሪካ ህጻናት ቁጥር ከአውሮፓ በ4 እጥፍ ይበልጣል
የአፍሪካ አገራት የህዝብ ቁጥር ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚገኝና፣ ፍጥነቱ በዚሁ ከቀጠለ እ.ኤ.አ በ2050 ከአለማችን አጠቃላይ ህዝብ ሩብ ያህሉ አፍሪካውያን ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ፣ ከትናንት በስቲያ ይፋ ባደረገው አዲስ የጥናት ውጤት እንዳስታወቀው፣ በአሁኑ ወቅት 1.2 ቢሊዮን የሆነው የአፍሪካ አጠቃላይ የህዝብ ቁጥር፣ በመጪዎቹ 30 አመታት ጊዜ ውስጥ 2.5 ቢሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ 580 ሚሊዮን ያህል ህጻናት እንዳሉ የጠቆመው ጥናቱ፤ ይህ ቁጥር ከአውሮፓ ጋር ሲነጻጸር በአራት እጥፍ እንደሚበልጥና በፈረንጆች አቆጣጠር በ2100 ከአለማችን አጠቃላይ ህጻናት መካከል ግማሹ አፍሪካውያን ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክቷል፡፡
አፍሪካ ከተፋጠነው የህዝብ ቁጥር እድገት ጋር የሚመጣጠን የተማረ ሃይልና ባለሙያ ካላፈራች የከፋ ችግር ውስጥ ትገባለች ያለው ጥናቱ፤ አህጉሪቱ የአለም የጤና ድርጅትንና አለማቀፍ የትምህርት ጥራት ደረጃዎችን ለማሟላት ተጨማሪ 5.6 ሚሊዮን የህክምና ባለሙያዎችንና 5.8 ሚሊዮን መምህራንን ማፍራት ይጠበቅባታል ብሏል፡፡

ምንጭ አዲስ አድማስ ጋዜጣ

The post በ2050 ከአለማችን ህዝብ ሩብ ያህሉ አፍሪካውያን ይሆናሉ ተባለ appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles