የአርጎባ ማህበረሰብ፣ በኢትዮጵያ በሰሜን ትግራይና ወሎ፣ በደቡብ ባሌ በምስራቅ ሐረር ቆላማ ስፍራና አፋር፣ ሰሜን ሸዋ አካባቢ የሚኖሩ የእስልምና ተከታዮች ናቸው፡፡ አርጎባዎች በኤርትራም እንደሚኖሩ ሲጠቆም “ጀበርት” የሚል መጠሪያ አላቸው፡፡ “አርጎቦ” የብሔረሰብ እና የቋንቋ መጠሪያ ነው፡፡
በ13ኛው ክፍለ ዘመን የይፋት ወላስማ ሥርወ መንግሥት ንግድን መሥርቶ በነበረ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን እስላማዊ መንግሥትን እንዳቋቋመ የሚገለጸው በኋላም በሁለተኛው ሂጅራ በነብዩ መሐመድ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከቁረሾች ጋር በነበረው ግጭት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ አረቦችን ተቀብሎ ያስተናገደ የመጀመሪያው የሙስሊም ማህበረሰብ የአርጎባ ማህበረሰብ እንደሆነም ይጠቁማሉ፡፡
“አርጎብኛ” የሴሜቲክ ቋንቋ ዝርያ ሲሆን በውል የተለዩ ሁለት ዘዬዎች አሉት፡፡ የመጀመሪያው በደቡብ ወሎ ከሚሴና ሾንኬ የሚነገረው “ሾንኬ ጦልሃ” እና በአፋር ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳ የሚነገረው “ሸዋሮቢታ ልዩ አምባ ዘዬ” በመባል ይታወቃሉ::
ከሰሜን እስከ ደቡብ ምስራቅ ተበታትነው የሚገኙት አርጎባዎች ሙሉ በሙሉ የእስልምና እምነት ተከታዬች ሲሆኑ “አርጎባ” የሚለው የብሄረሰቡ መጠሪያ ስያሜ
እንደ አካባቢው ነዋሪዎች እምነት “አረብ ገባ” ለማለት የተፈለገ ነው፡፡
እንደ ጥናቶች ግን “የአርጎባ ህዝብ በኢትዮጵያ ይኖር የነበረ ጥንታዊ ህዝብ መሆኑንና እስልምናን በተለያዩ ጊዜዎች የተቀበለ ያስፋፋ ህብረተሰብ ነው” በሚል የተቀበለ ያስፋፋ ህብረተሰብ ነው” በሚል ይገለፃል::
የአርጎባ ማህበረሰብ መተዳደሪያው ከሆነው ንግድ፣ እርሻና የሽመና ስራ ከኢትዮጵያ የመን ድረስ በመጓጓዝ ትስስሩ በጋብቻም ተዋልደዋል:: በሾንኬና አርጎባዎች በሚኖሩበት አካባቢ የልጅ ልጆቻቸው ይገኛሉ፡፡
አርጎብኛ ከቋንቋው በተጨማሪ የማህበረሰቡ መገለጫ የሆኑ የሰርግ፣ የሐዘን፣ የአመጋገብ ስረዓቶቻቸው፣ ለቱሪስት መስህብነት ከፍተኛው ድርሻ ያለው ሲሆን የተለየ ጥበብ ያረፈባቸው እና ከአንድ ሺህ ዓመት በላይ ያስቆጠሩ የመኖሪያ ቤቶች፣ መስጊዶቻቸው ባህላዊ የስነ ጥበብ ህንጻ ውበት ጥንታዊውን፣የታሪክ፣ የቋንቋ፣ የእምነት፣ የአኗኗር ፍልሥፍና የሥልጣኔ ዘመን ያስታውሳሉ፡፡
The post የአርጎባ ማህበረሰብ appeared first on Bawza NewsPaper.