በውድ ኢትዮጵያዊነታቸው የምናውቃቸው እና በኢትዮጵያዊነት አቀንቃኝነታቸው የምንደነቅባቸው፥ ክቡር ኢትዮጵያዊው ሊቅ፣ አባት እና አገር ወዳድ፣ “ኢትዮጵያ የዓለሙ መፋረጃ”ን እና ሌሎች ከአስር የሚበልጡ መጽሐፍትን በማሳተም ለንባብ ያደረሱ (እንዲሁም ያልታተሙ ሥራዎችም እንዳሏቸው ሳይዘነጋ)፣ በሀይማኖቱም፥ መጽሐፍ ቅዱስን ኢትዮጵያዊ መልክ እና ቅርጽ ለማስያዝ በመድከም የሚታወቁት፥ ንቡረ ዕድ ኤርሚያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሥጋ ተለይተውናል።
በመጽሐፍት ከደረሱን ባሻገር፥ Ethiopia The Kingdom of God የሚል ድረ ገጽ ላይ በመጦመር፣ በአኗኗራቸውና በየሁኔታው ኢትዮጵያዊነትን በመተረክ እናውቃቸዋለን። ከመጽሐፍቶቻቸው መካከልም…
1. ምናሴ የመከራየ ደስታ አለምን ረታ
2. Ethiopia: The Classic Case
3. ኢትዮጵያ የዓለሙ መፋረጃ
4. ኢትዮጵያዊው በማንነቱ ፍለጋ
5. ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት (1)
6. ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት (2)
7. ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት (3)
8. ምሥራች! ከእናት ኢትዮጵያ! ለኢትዮጵያ ልጆች ስለኢትዮጵያዊነት።
9. ኢትዮጵያ የዓለሙ መፋረጃ
10. አዳምና ሔዋን በኢትዮጵያ – ፩
11. አዳምና ሔዋን በኢትዮጵያ – ፪
12. ለኢትዮጵያ ሕጻናት (የቅዱሱ ኪዳን ሥርዓተ ትምህርት በግዕዝ እና በዐማርኛ) አንደኛ መጽሐፍ
የሚያልሟትን እና ሲለፉላት የኖሯትን ኢትዮጵያ እኛ ብንቀር ልጆቻችን ይኖሩባት ዘንድ፣ ለቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመድም መጽናናት ይኾን ዘንድ እንመኛለን።
ነፍሳቸውን በቀኙ ያሳርፍልን!
Yohanes Molla Facebook page
The post One of the most highly acclaimed Ethiopian philosophers Ermias Kebede passed away appeared first on Bawza NewsPaper.