ማታ ላይ ለአቶ ባል መልዕክት ይደርሰዋል፤ በስልክ፡፡
:
ባልም ለወይዘሮ ሚስት “ነገኮ ዘመዶቼ እንመጣለን አሉኝ …” ብሎ የሰማውን ያጋራል፡፡ ሚስትም ተበሳጭታ …
:
ሚስት፦ “ቆይ ለምንድነው የሚመጡት …”
ባል፦“እሱንማ እኔ ምን አውቃለሁ … ጉዳይ ይኖራቸው ይሆናላ፤ ብቻ በሰላም ነው ብለውኛል …”
.
ሚስት፦ “ስንት ሆነው ነው የሚመጡት?”
ባል፦“እሱንስ አልጠየኳቸውም … እንዲሁ እንመጣለን ሲሉ እሺ አልኩ እንጂ …”
ሚስት፦“ታዲያ የመጡ እንደሆነሳ?”
ባል፦“አይ! … እንድንዘጋጅ ብዬ ነው፡፡
.
መቼስ እንግዳ ሲመጣ ዝም አይባል …”
ሚስት፦“እኔ ምንም የማዘጋጀው የለኝም … ቤቱን እንደሆነ ያውቁታል … አዲስ አይደሉም … ”
.
ባል፦“የሚገዛም ነገር ካስፈለገም ልገዛዛና ሰርተን እንጠብቃቸው እንጂ”
ሚስት፦“ምንም አያስፈልግም … ያለውን ይቀምሳሉ”
ባል፦“ምን አለ …”
.
ሚስት፦ “ውሃስ ቢሆን … ሌላ የማዘጋጀው የለኝም!”
ባል፦“ኧረ ተይ … ሰው አለን ብለው አይደል ወደኛ መምጣታቸው … እንደገቡ እንኳ የሚቀማምሱት ብናዘጋጅ አይሻልም …”
ሚስት፦“ይምጡና ያለውን አቀርብላቸዋለሁ …”
.
.
ይችኑ እንደተባባሉ ነጋ፡፡ ባልም በማለዳ ተነስቶ የቤቱን ሁኔታ ሲያይ ምንም የለም … ቁርስም የለም … ጭጭ … ጭጭ … ሚስትም ለጥ ብላ እንደተኛች አረፈደች፡፡
ባል ሹልክ ብሎ ወጣ፡፡ ወዲያው የሚስት እናት፣ አባት እና ሌሎችም ተሰባስበው ከተፍ አሉ፡፡ ደንግጣ ተነስታ ተቀበለቻቸውና ወደ ባል ደወለች …
.
ሚስት፦“ለምንድነው ዘመዶችሽ ይመጣሉ ብለህ ያልነገርከኝ”
ባል፦“እንዴ! ነገሬሽ …”
ሚስት፦ “ዘመዶቼ ይመጣሉ ነውኮ ያልከኝ!”
ባል፦“አዎ! ያው ያንቺ ዘመዶችስ የኔ ማለት አይደሉ እንዴ!”
ሚስት፦“እሺ አሁን ምን ላድርጋቸው”
ባል፦“ሌላ ምን ታደርጊያቸዋለች አስተናግጃቸው እንጂ”
ሚስት፦“የተዘጋጀ ደህና ነገር የለማ”
ባል፦“ታዲያ ምን ይሻላል?”
ሚስት“በቃ … ከምግብ ቤትም ቢሆን የሚበላ ነገር ገዛዝተህ ና እንጂ …”
ባል፦“እኔ እንኳ አሁን መምጣት አልችልም፤ እቆያለሁ … አንቺን ምን አስጨነቀሽ … ለቤቱ እንደሆነ አዲስ አይደሉ … ያለውን ነገር ስጫቸው”
.
ሚስት፦“ምንም ነገር የለምኮ!”
ባል፦“ … ውሃም ቢሆን ስጫቸው … ባይሆን ቁልፉን ለጎረቤት ሰጥተሽልኝ አብረሻቸው ሂጂ፡፡”
ጠንቋይ እና ቀልዱ ሀሀሀሀ Page
The post ውሃም ቢሆን ስጫቸው … ባይሆን ቁልፉን ለጎረቤት ሰጥተሽልኝ አብረሻቸው ሂጂ፡፡” appeared first on Bawza NewsPaper.