Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

አርቲስት መስፍን ጌታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

$
0
0

አርቲስት መስፍን ጌታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!

የዙምራ ፊልም፣ የሰው ለሰው እና የዘመን ድራማ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ደራሲና ተዋናይ የነበረው አርቲስት መስፍን ጌታቸው ህይወት አልፏል።

አርቲስት መስፍን ጌታቸው በርካታ የጥበብ ስራዎችን በድርሰት፣ በአዘጋጅነት እና በትወና ለአገሩ ያበረከተ ሁለገብ ባለሞያ ነበር።አርቲስቱ በኢትዮጵያ ሬድዮ ዝነኛ የነበረው የቀን ቅኝት ድራማ ደራሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው የሰው ለሰው ተከታታይ ድራማ ደራሲ እና ተዋናይ ነበር።

አርቲስት መስፍን ጌታቸው የዙምራ ፊልም፣ መንታ መንገድ የሬድዮ ተከታታይ ድራማ እና ሌሎችም ሥራዎችን በተለያዩ የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ለህዝብ ማድረስ ችሏል።

አርቲስት መስፍን ጌታቸው ባለትዳር እና የሦስት ልጆች (የሁለት ሴት እና የወንድ ልጅ) አባት ነበር።ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ እና አድናቂዎች ልባዊ መጽናናትን እንመኛለን፡፡

The post አርቲስት መስፍን ጌታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ appeared first on Bawza.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles