Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

ይህንን ምስል አየሁና ለረጅም ጊዜ በሃሳብ ጭልጥ አልኩኝ…

$
0
0

By sileshi Teka

ይህንን ምስል አየሁና ለረጅም ጊዜ በሃሳብ ጭልጥ አልኩኝ… በምን እና እንዴት እንደምገልጸውም ግራ እስክጋባ ድረስ… እንደገና ተመለከትኩት አሁንም ለረዥም ጊዜ ያናግረኝ ጀመር።

አስተውሎ አለመጓዝን ሳስብ በድንገት(Accidentally) የተከሰተ ቢሆንስ እሚል እሳቤ ከተፍ ይላል…. በሌላ በኩል ደግሞ የብቸኝነት መጨረሻው ብዩ ሳስብ ከመንጋዎቹ መሃከል ወግተው(ገፍተውት) ቢሆንስ የሚል ሹክሹክታ ይሰማኛል… ብቻ ምስሉን ለተመለከተው ብዙ ነገራቶች አእምሮው ላይ እንዲመላለሱ ያደርጋል። 

ብቸኝነት….. ረዳት ማጣት….. የምንጓዝበት መንገድን አለመምረጣችን…ለነገሮች ያለን ትኩረት አናሳነት…. አወዳዳቃችንን አለማወቃችን…. ከወደቅን በኋላ ለመነሳት መጣርን ፤ የሚያነሳን ፤ የሚረዳን ማጣትን ወይም ቀድመን አለማሰብን…. በሰዋዊ ስንተረጉመው

በአጠቃላይ ግን አንዳችን ለአንዳችን መቼና እንዴት #እንደምናስፈልግውአናውቀውም የሚለውን ደመደመልኝ…. 

ስለሆነም ትናንት የራስህ ጉዳይ ያልነው አካል ምናልባት ዛሬ ላይ የህይወታችን መትረፊያ ስበብ(ምክንያት) ሊሆን ይችላል 

ትናንት የገፋነው እንዲህ ባለ ሁናቴ ብንጠራው የመስማት እድሉ ኢመንት ሊሆን ይችላል… ታዲያ እንዲህ እንደ ዛሬ #የአንድነታችን_ችቦጭላንጭሉ ሊጠፋ በዳዴ ሲሄድ መሰል ነገራቶች እኛን አያስተምሩን ይሆን…? ምናልባት በዚህ ሁናቴ ረዳት በለለበት እርስዎ ቢሆኑስ እሚል እሳቤ ጫረብኝ….?

እናም ሞትን(መጨረሻችን) ሳስብ እንዲህ አልኩኝ…

የመኖር ጊዜያችን ቀኗ ተገድባ
በቦታ’ና ስአት በገዳይ ተውባ
መርህን ለመፈጸም ትጠብቀናለች የ’ኛን በየተራ
በሞቱ መላይካ እንደየስራችን ቅጽበት ሳትራራ

አትፈትነን ይሻላል….!!!

The post ይህንን ምስል አየሁና ለረጅም ጊዜ በሃሳብ ጭልጥ አልኩኝ… appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles