Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 7 ሺሕ 520 ተማሪዎችን አስመረቀ።

$
0
0

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 7 ሺሕ 520 ተማሪዎችን አስመረቀ።ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 23/2012 ዓ.ም (አብመድ) የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና መደበኛ ባልሆነ መርሀ ግብር ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 7 ሺሕ 520 ተማሪዎች ዛሬ ቅዳሜ አስመርቋል።

የዩቨርሲቲው ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ዘውዱ እምሩ (ዶክተር) የምረቃ ሥነ ስርዓቱ ጥቂት ተማሪዎችን ፊት ለፊትና አብዛኛዎቹን ባሉበት በተለያዩ አማራጮች በቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብሮች ታግዞ ማስመረቁን ተናግረዋል።ተመራቂዎቹ በህክምናና ጤና ሳይንስ፣ በስነ-ህንጻ (አርክቴክቸር) እና በአውቶሞቲቭ ምህንድስና በመደበኛውና በሌሎች ተከታታይ መርሀ ግብሮች ያስለጠናቸው 4 ሺሕ 543 ተማሪዎች ናቸው፡፡

በድኅረ መርቃ መርሀ ግብር በሁለተኛ ዲግሪ በመደበኛውና በተከታታይ መርሀ ግብር ደግሞ 2 ሺሕ 254 ተማሪዎች፣ በሦስተኛ ዲግሪ መርሀ ግብር 40 ተማሪዎች፣ እንዲሁም በስፔሻሊቲ መርሀ ግብር 41 ተማሪዎች፣ በሰርቲፊኬት መርሀ ግብር 642 ተማሪዎች ናቸው።

ከተመራቂዎች መካከል 2 ሺሕ 345 ሴቶች ናቸው፤ ከነዚህ ሴት ተመራቂ ተማሪዎች መካከል አምስቱ የሶስተኛ ዲግሪ ተመራቂ ናቸው፡፡ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃ 92 ፕሮግራሞች፣ በድህረ ምረቃ (ማስተርስ) 153 ፕሮግራሞች፣ በፒኤችዲ 59 ፕሮግራሞች፣ በስፔሻሊቲ 8 ፕሮግራሞች፣ እና በሰርቲፊኬት 4 ፕሮግራሞች አሉት፡፡ አብመድ 2012 ዓ.ም በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለተመረቁ ተማሪዎች ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles