በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,733 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል
—————————
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 18,766 የላብራቶሪ ምርመራ 1,733 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪም 586 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 48,140 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 758 ደርሷል፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 17,415 ደርሷል።