Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

የኢትዮጵያ ሳተላይት በቀን 40 ሺህ ዶላር ግምት ያለው መረጃ አንደምትልክ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

$
0
0

የኢትዮጵያ ሳተላይት በቀን 40 ሺህ ዶላር ግምት ያለው መረጃ አንደምትልክ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ ባሕር ዳር፡ ሰኔ 08/2012 ዓ.ም (አብመድ) ሳተላይቷ በሚሰጣት ትዕዛዝ መሠረት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ክትትል በማድረግ መረጃ እንደምታደርስ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬተር ሰሎሞን በላይ (ዶክተር) ለአብመድ ተናግረዋል፡፡ ሁለተኛውን የዓለም ጦርነትን ተከትሎ የፉክክር መድረክ መሆን የጀመረው የሕዋ ምርምር አሁንም የሀገራት የቴክኖሎጂ ደረጃ መመዘኛ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡ ኢትዮጵያም ከብዙ መዘግዬት በኋላ ዘርፉን ተቀላቅላለች፤ ለዘርፉ ተወዳዳሪነትም ሌት ተቀን እየተጋች ነው፡፡ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ደግሞ ይህንን ዘርፍ እየመራ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደሕዋ ያመጠቀቻት ሳተላይት በስኬት ሥራዋን እያከናወነች ነው፡፡ የኢንስቲትዩት ዋና ዳሬክተር ሰሎሞን በላይ (ዶክተር) ‘‘ሳተላይቷበቀን አራት ጊዜ በሚፈለገው አቅጣጫ ውጤታማ መረጃ እያቀበለች ነው’’ ብለዋል፡፡ በ24 ሰዓታት ውስጥ 40 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚገመት መረጃ ሳተላይቷ እያቀበለች እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ ዶክተር ሰሎሞን ስለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሲያስረዱም ግድቡ የዛሬ ብቻ ሳይሆን የነገ ኢትዮጵያውያን ጭምር በመሆኑ ‘‘የጉባው የኃይል ማመንጫ ነጭ የደም ሕዋስ ነው’’ ብለዋል፡፡ ለሳተላይቷ ትዕዛዝ በመስጠት ግድቡን በሚመለከት መረጃ አንድትልክ እየተደረገ ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡ ስለግድቡም ሆነ ስለሚፈለገው ማንኛውም መረጃ ሳተላይቷን በማዘዝ መረጃ እየተሰበሰበ እንደሆነና የግድቡን ደኅንነት በሚመለከትም አስፈላጊውን መረጃ ተቋሙ እየተቀበለ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡ በቅርቡ የኮሙዩንኬሽን ሳተላይት የማምጠቅ ዕቅድ ያለው ተቋሙ በ15 ዓመት ውስጥ ቢያንስ 10 ሳተላይቶቸን ወደሕዋ ለማምጠቅ ዕቅድ ይዟል፡፡ በአፍሪካ ካሉ የሕዋ ምርምር ተቋማት ውስጥ ተወዳዳሪ መሆን የቻለው ኢንስቲትዩቱ ዘርፉን የሚመራ ፖሊሲ እና ስትራቴጅም ማጽደቁን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ወደፊት ቀጣይ የሀገሪቱ መመኪያ ይሆን ዘንድ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የተለያዩ ተመራማሪዎችን በማሰልጠን ላይ ነው፡፡

ከአማራ ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ

ዘጋቢ፡- አንዷለም መናን


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles