በማንኛም የክብደት መጠን ያሉ ፈጠን ብለው የሚራመዱ ሰዎች ዝግ ብለው ከሚራመዱት እስከ 15 ዓመታት ረዘም ያለ ዕድሜ እንደሚኖራቸው አንድ ጥናት አመልክቷል፡፡
በሌስተር ዩኒቨርሲቲ የሚሠሩ ተመራማሪዎች እ.ኤ.አ ከ2006 እስከ 2016 በዩናይትድ ኪንግደም ባዮባንክ ዕድሜያቸው በአማካይ 52 ዓመት በሆኑ 474,919 ሰዎች ላይ ጥናት አካሂደዋል፡፡
ፈጠን ብለው የሚራመዱ ሴቶች ከ86.7 እስከ 87.8 አመት ሲኖሩ ወንዶቹ ደግሞ ከ 85.2 ወደ 86.8 ዓመት መኖር ችለዋል ተብሏል ጥናቱ፡፡
በሌላ በኩል ዝግ ብለው የሚራመዱ ሴቶች እስከ 72.4 ዓመት ዕድሜ መኖር የቻሉ ሲሆን የወንዶቹ ደግሞ 64.8 ዓመት ሆኗል ፡፡
ጥናቱ የተሰራው በፍጥነት የሚራመዱትንና የማይራመዱትን በማነጻጸር እንጂ ፈጠን ብለው የሚጓዙ ሰዎች ረጅም እድሜ ይኖራሉ ማለት እንዳልሆነ ተነግሯል፡፡
የጤና ባለሙያዎች ለህመምተኞቻቸው ከሌሎች መፍትሄዎች በተጨማሪ ፈጣን የእግር ጉዞ ማድረግን ማዘዝ እንደሚገባቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ጠቁመዋል፡፡