በእግሮቿ ብቻ አውሮፕላን የምታበረው ጄሲካ ኮክ በዓለም ዙሪያ በአቬሽን ዘርፉ ለሴቶች ተምሳሌት ሆናለች፡፡
“ሌሎች አብራሪዎች በእጃቸው የሚያደርጉትን እኔ በእግሮቼ በመተካት በማድረግ እችላለሁ::” ትላለች ጂሲካ፡፡
በአሜሪካ አሪዞና ተወላጅ የሆነችው ጄሲካ ኮክስ ስትወለድ እጆች አልነበሯትም፡፡ “እናቴ ጤናማ የእርግዝና ጊዜ ነበራት” የምትለው ጄሲካ ያለእጅ መወለዷ ለቤተሰቦቿ እጅግ አስደንጋጭ እንደነበርና በተለይ እናቷ ዶክተሮቹ “ልጅሽ ምንም እጆች የላትም” ብለው ሲሰጧት እጅግ ተጎድታ እንደነበር ትናገራለች፡፡
በእድገቷ ላይ ጉድለት ተሰምቷት እንደማያውቅ ጄሲካ ትናገራለች፤ ለዚህም ቤተሰቦቿ ለሰጧት ጥንካሬ እና ማበረታቻ ታመሰግናለች ፡፡
በልጅነቷ በአይሮፕላን ማብረር በጣም ትፈራ እንደነበር ጄሲካ ታስታውሳለች ፡፡
አንድ እለት ግን ነገሮች ሁሉ ተቀየሩ በአነስተኛ አውሮፕላን ስትጓዝ ፓይለቱ ከፊት እንድትቀመጥ ይጋብዛታል፡፡ አይሮፕላኑ ሁለት መቆጣጠሪያዎች ብቻ ነበሩት ፓይለቱ እጆቹን ከመቆጣጠሪያው ላይ በማንሳት እንድታበር ያደርጋታል፡፡ “ምንም እንኳን ነገሮች አስፈሪ ቢሆኑም ፊት ለፊት መጋፈጡ በጣም ጠቃሚ ነው” ትላለች ጄሲካ ፡፡
ጄሲካ እ.አ.አ በ2005 ከአሪዞና ዩኒቨርስቲ እንደተመረቀች ፓይለት ለመሆን ስልጠና ጀመረች፡፡
ጄሲካ ሁሉንም ነገር ለማወቅ ሶስት አመት እንደወሰደባት ትናገራለች ፡፡
ከዚህ ሁሉ በኃላ ጄሲካ እ.ኤ.አ. በ 2008 በፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ቀለል ያለ የስፖርት አውሮፕላን እንድታበር ሰርተፍኬት እንደተሰጣት ሴ.ኤን.ኤን አስነብቧል፡፡