Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

ወደ ትምህርት በማይመለሱ የህክምና ሙያ ተማሪዎች እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለፀ

$
0
0

ከሰኞ ጀምሮ ወደ ትምህርት በማይመለሱ የህክምና ሙያ ተማሪዎች እርምጃ እንደሚወሰድ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የመጨረሻ አመት (ኢንተርን) ተማሪዎችና ስፔሻሊቲ (ሬዚደንት) ተማሪዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ውይይት ከተካሄደ በኋላ ላነሷቸው ጥያቄዎች እርምጃዎች እንደተወሰዱ ነው ያስታወቀው፡፡

ምላሽ ላላገኙ ጥያቄዎችም በዝርዝር አጥንቶ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት አራት ግብረ ሃይል ተቋቁመው ወደ ስራ መግባቱን ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡

ሆኖም አሁንም በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ያቋረጡ ተማሪዎች አሉ ሲል ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ተማሪዎች ተገንዝበው በፍጥነት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በማለት አሳስቧል፡፡

ከሰኞ ጀምሮ ወደ ትምህርታቸው የማይመለሱትን ተማሪዎች ተቋማት ባላቸው የአካዳሚክ ህግ ቀጣይ እርምጃ እንዲወስዱ መመሪያ መተላለፉን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles