Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

የናይጄሪያ ምርጫ ተራዘመ

$
0
0

የናይጄሪያ ምርጫ ወደሚቀጥለው ሳምንት ተሸጋግሯል።

የናይጄሪያ ምርጫ ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም እና ማጭበርበር ሊያንዣብብበት ይችላል የሚሉ ጥርጣሬዎች በርካቶች ናቸው፡፡ ሆኖም ፕሬዝዳንት ሙሃመዱ ቡሃሪ መንግስታቸው ነፃ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ ምርጫ እንደሚያደርግ አረጋግጥላችኋለሁ ሲሉ በድጋሚ ተናግረዋል፡፡

የመሪው ቡሃሪ ኦል ፕሮግረሲቭስ ኮንግረስ ፓርቲና ተፎካካሪው የህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ምርጫውን ለመቆጣጠር እየተሴረ ነው በሚል እርስ በርሳቸው ይወነጃጀላሉ፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንታዊና ፓርላመንታዊ ምርጫ በአንድ ሳምንት መዘግየቱን ያስታወቀው ገለልተኛው ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽን ነው፡፡

በታቀደው መሰረት በምርጫው ሂደት መቀጠል ሊሳካ የሚችል አይደለም ያሉት የምርጫ ኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ማህሙድ ያኩቡ የምርጫ ጣቢያዎች ሊከፈቱ አምስት ሰአታት ሲቀሩት መራዘሙን አሳውቀዋል፡፡

ነፃና ፍትሃዊ ምርጫን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ውሳኔ ያስፈልጋል ሲሉም ገልፀዋል፡፡ 
(አብመድ)


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles