Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረክ አየተካሄደ ነው

$
0
0

ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረክ አየተካሄደ ነው።

የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረክ በኢንተር ኮንቲነታል ሆቴል እየተካሄደ ሲሆን፥ የምክክር መድረኩ ባለፈው ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተዘጋጅቶ የነበረው ውይይት 2ኛ ምዕራፍ ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ነጻ፣ ፍታዊና ታመዓኒ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ የፖለቲካና የህግ ለውጦች መከናዎናቸውን ለማረጋገጥ ፣ የዴሞከራሲ ተቋማትን ለመገንባት፣ በተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ሊኖር የሚገባውን ትብብር ለማጠናከርና ተፎካካሪ ፓርቲዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው የጋራ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ሃሳቦችን ለማዳበር ምክክር ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።

ፓርቲዎቹ በጽሁፍ ለምርጫ ቦርድ ያቀረቧቸውንና ወደፊትም የሚያቀርቧቸው አጀንዳዎችን የቦርዱ ሰብሳቢና ቦርዱ በሚያቋቁመው የድጋፍ ኮሚቴ አማካኝነት በቅደም ተከተል ለውይይት አቅርበው ያጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የዘገበው ኤፍቢሲ ነው::

 

The post የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረክ አየተካሄደ ነው appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles