ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 06/2011 ዓ.ም (አብመድ) የአፍሪካ ሊደርሺፕ ሜጋዚን የአወውሮፓውያኑ 2018 የአፍሪካ ምርጥ ሰዎችን ምርጫ አካሂዷል፤ በውጤቱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር. ዐብይ አህመድ አሸንፈዋል፡፡
ዶ.ር ዐብይ በጠቅላላ መራጮች ከተሰጠው ድምጽ ከ85 ከመቶ በላይ ድጋፍ በማግኘት መመረጣቸውም ታውቋል፡፡
በሰባት ዘርፎች በተደረገው ውድድር 123 ሺህ 446 መራጮች በመጽሔቱ ድረ ገጽ፣ 33 ሺህ መራጮች በመጽሔቱ ማኅበራዊ ገጽ እና ሦስት ሺኅ 400 መራጮች ደግሞ በኢ-ሜይል ድምጽ መስጠታቸውን የዝግጅት ክፍሉ አስታውቋል፡፡
የውድድሩ አሸናፊዎች በመጪው የካቲት ወር አጋማሽ በደቡብ አፍሪካ ጁሀንስበርግ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ሺልማታቸውን እንደሚቀበሉም ታውቋል፡፡
አሸናፊዎቹም፡-
• የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ.ር ዐብይ አህመድ
• የዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ ሴት መሪ ናይጀሪያዊቷ የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ጄ መሀመድ
• በትምህርት ዘርፍ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ናይጀሪያዊው መሀመድ ኢንዲሚ፣ ኦሬንታል ኢነርጂ
• የዓመቱ አፍሪካዊ ምርጥ ሥራ ፈጣሪና ቀጣሪ ናይጀሪያዊው አቲኩ አቡበከር
• በፖለቲካዊ አመራር የዓመቱ ምርጥአፍሪካዊ የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ
• በበጎ አድራጎትና ለማኅበረሰብ ጉልህ አስተዋጽኦ በማበርከት የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ናይጀሪያዊውቶኒ ኢሉሜሉ፣ ሄይርስ ሆልዲንግ
• የዓመቱ አፍሪካዊ ምርጥ ወጣት የቦትስዋናው የኢንቨስትመንት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቦጎሎ ጆይ ኬንወንዶ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
የአፍሪካ ሊደርሽፕ መጽሔት በእንግሊዝ ሀገር ሕጋዊ ዕውቅና ኖሮት የሚታተምና አፍሪካዊ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ለዓለማቀፍ አንባቢዎቹ የሚያስተዋውቅ መጽሔት ነው፡፡ መጽሔቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዓለማቀፍ ኢንቨስተሮች፣ የንግድ ድርጅቶች ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የመንግሥታት ፖሊሲ አውጭዎች፣ ዓለማቀፍ ድርጅቶች ደንበኞች አሉት፡፡ ደንበኞቹ በአፍሪካ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ እስያ፣ አውሮፓና አሜሪካ የሚገኙ ናቸው፡፡ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችም ከ900 ሺህ በላይ ቋሚና የተመዘገቡ ደንበኞች አሉት፡፡
ምንጭ፡- አፍሪካን ሊደርሺፕ ሜጋዚን
በአብርሃም በዕውቀት
http://africanleadership.co.uk/breaking-prime-minister-abi…/
The post ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ‹‹ የዓመቱ የአፍሪካ ምርጥ ሰው›› ተብለው ተመረጡ፡፡ appeared first on Bawza NewsPaper.