የአማራ ክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ለመወያየት ሕዝባዊ ስብሰባ ያደርጋል።
ቀን፡ SUNDAY, DECEMBER 2nd, 2018
ሰዓት፡ 1:30PM
ቦታ ፡ ፣ HILTON MARK CENTER
5000 SEMINARY RD
ALEXANDRIA, VA 22311
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 18/2011ዓ.ም (አብመድ) የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ናቸው ወደ ሰሜን አሜሪካ የሚያመሩት፡፡
የጉዞው ዓላማ በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ከሚገኙ የአማራ ተወላጆች (በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ብሄርና ብሄረሰቦችን ያካተተ) እና በአማራ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ለመወያየት ነው፡፡
በክልሉ ኢንቨስትመንት፣ቱሪዝም፣ መልካም አሥተዳደር እና ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ መምከር ደግሞ በውይይቱ ትኩረት የሚደረግባቸው ነጥቦች እንደሚሆኑ ነው የሚጠበቀው፡፡
ምንጮቻችን እንዳረጋገጡልን በውይይቱም የተሻለ መቀራረብን በመፍጠር ኢትዮጵያዊያኑ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ በአማራ ክልል ልማት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ይደረጋል፡፡ ልዑኩ የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 22/2011 ጉዞውን እንደሚጀምር ይጠበቃል፡፡
Source: የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ
The post የአማራ ክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ለመወያየት ሕዝባዊ ስብሰባ ያደርጋል! appeared first on Bawza NewsPaper.