አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ መንግስት 330 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ወታደራዊ መሳሪያዎች ሽያጭ ለመፈፀም መወሷና የተነገረ ሲሆን፥ ወሳኔዋ ቻይናን አስቆጥቷል።
ራስ ገዝ የሆነውችና ቻይና የራሴ ግዛት ናት ብላ የምታስባት ታይዋን ከአሜሪካ ጋር በደረሰችው የወታደራዊ መሳሪያ ሽያጭ ስምምነት መሰረት የኤፍ 16 ተዋጊ ጀትና የሲ 130 ካርጎ አውሮፕላንን ጨምሮ የተለያዩ የአውሮፕላን መለዋወጣጫዎች ይቀርብላታል ተብሏል።
ቻይና በበኩሏ አሜሪካ ሽያጩን እንድትሰርዝ ያስጠነቀቀች ሲሆን፥ ሽያጩን ካልሰረዘች የሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት አደጋ መሆኑን አስታውቃለች።
የቻይና መከላከያ ሚኒስትር ሽያጩ ፥ በቻይና ሀገራዊ ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንደሆነ በመግለፅ ልዓላዊነትንና ደህንነትን የሚጎዳ ድርጊት ነው በማለት ገልጿል።
ቻይና በፈረንጆቹ 1979 ያሳለፈችውን ውሳኔ አሜሪካ በመተላለፍ ከታይዋን ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከሯ ይገለፃል።
የአሜሪካ ውሳኔ የመከላከያ ሀይሏን እንደሚያጠናክርላት የገለፀችው ታይዋን የአሜሪካን እርምጃ ማድነቋ ተገልጿል።
ምንጭ፥ አልጀዚራ
The post አሜሪካ ለታይዋን 330 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ወታደራዊ መሳሪያ ለመሸጥ መወሰኗ ቻይናን አስቆጣ appeared first on Bawza NewsPaper.