Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

ማህበራት ለቤት መስሪያ ቦታ ዕጣ ሊያወጡ ነው፡፡

$
0
0

ማህበራት ለቤት መስሪያ ቦታ ዕጣ ሊያወጡ ነው፡፡

ባሕር ዳር፡መስከረም 11/2011 ዓ.ም(አብመድ) የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ለማግኘት ከተደራጁና ዕውቅና ካገኙ ማኅበራት መካከል ለመምህራንና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሊሰጥ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የዝግጅት ክፍላችን ከተለያዩ ታማኝ ምንጮች እንዳረጋገጠው በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቦታ ለማግኘት የተመዘገቡና ዕውቅና ያገኙ የመምህራንና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ማኅበራት መስከረም 12 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ የሚያወጡ ይሆናል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ ዕውቅና ከተሰጣቸው ከአንድ ሺህ በላይ ማኅበራት ይገኛሉ፡፡

ከነዚህ መካከል በአሁኑ ማስታወቂያ መሰረት ቦታ የሚያገኙት አባሎቻቸው መምህራንና የመከላከያ ሠራዊት አባላት የሆኑ 58 ብቻ ናቸው፡፡ የመምህራን የመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት 51 ናቸው፡፡ ሰባቱ ማኅበራት ደግሞ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ናቸው፡፡

ስለ ሌሎች ኅብረት ሥራ ማኅበራት የቦታ አሰጣጥ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ Amhara Mass Media Agency

 

The post ማህበራት ለቤት መስሪያ ቦታ ዕጣ ሊያወጡ ነው፡፡ appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles