Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Oromo music legend Artist Mohammed Tewil quiet music

$
0
0

Ethiopian artist Mohamed Tewil,  a known oromo music legend  announced on Seifu Fantahun show  yesterday April 29, 2018 that he quit music and started following a spiritual journey(Muslim). In addition, He cut his dreadlocks and burned with all his music records to look the real mohamed. Here is his interview with Bawza Newspaper 10 years back about his biography and music work.

Mohamed Tewil ( Bawza Photo)

የዛሬው የባውዛ የኪነጥበብ ባለሙያ እንግዳችን አርቲስት መሀመድ ጠዊል ይባላል። የኪነጥበብ ዙሪያውና የህይወት ገጠመኙን እንዲነግረን በስልክ ቃለመጠይቅ አድርገንለታል።

ባውዛ፡- ጤና ይስጥልን አርቲስት መሀመድ ጠዊል በመጀመሪያ ፈቃደኛ በመሆንህ በባውዛ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ስም ልናመሰግን እንወዳለን፡፡

መሀመድ ጠዊል፡-እኔም ይህንን እድል በማግኝቴ በጣም ደስተኛ ነኝ

ባውዛ፡-  እስቲ ስለትውልድ አካባቢህና አስተዳደግህ ብታጫውተን

መሀመድ፡-  ተወልጄ ያደኩት በሀረር ክ/ሀገር አፈቴሳ በሚባል አካባቢ ነው፡፡ በ1963 ዓ.ም ከሀረር አዲስ አበባ መጣሁ

ባውዛ፡-  ሙዚቃ መቼና የት ነበር የጀመርከው

መሀመድ፡-  ሙዚቃ የጀመርኩት ክቡር ዘበኛ ውስጥ ነው በ1964 ዓ.ም በወታደርነት ተቀጥሬ ከገባሁ በኋላ

ኮርስ ደብረ ብርሀን እንደጨረስኩ ወደ ሙዚቃ ክፍል ተመደብኩ የተመለመልኩት በስፖርትና በሙዚቃ ነበር፡፡

ባውዛ፡-  የትኛው አመዘነ ስፖርት ወይስ ሙዚቃ

መሀመድ፡-  ሙዚቃ——-ሣቅ

ባውዛ፡-  ምን ዓይነት ስፖርት አዘውትረህ ትጫወት ነበር ከቁመትህ ርዝማኔ በመነሣት ልትጫወት የምትችለውን መገመት ይቻላል

መሀመድ፡-  መረብ ኳስ (ቫሊቮል)፣ ባስኬት ቦል፣ ሩጫ ዝላይ—- የመሳሰሉትን እጫወት ነበር ጦሩ ውስጥ—–ከዚያ በኋላ ወደ ሙዚቃ ክፍል ተዛውሬ በማርሽ ቡድኑን ዱላ ማሽከርከር ፊት ለፊት በመምራት አገለግል ነበር

ባውዛ፡-  በምን ቋንቋ ነበር የመጀመሪያ ዘፈንህን ያንጐራጐርከው

መሀመድ፡  እኔ  የመጀመሪያ  ቋንቋዬ  የኦሮምኛ  ነው፡፡  አብዛኛውንም  የምዘፍነው  በኦሮምኛ  ነው፡፡ አረብኛም በትክክል እሰማለሁ አወራለሁ፡፡ ሱዳንኛ የምዘፍነው አረብኛ ስለማውቅ ነው የሱዳን ዘፈን ደግሞ ሙዚቃውን  ስለምወደው በመድረክ ላይ ብዙውን ጊዜ እዘፍናለሁ፡፡ በካሴቴም ላይ አንዳንዶቹን ዘፋን አወጣቸዋለሁ፡፡ ካሉት ከነ ጥላሁን ገሠሠ፣ ከመሀሙድ አህመድ ከብዙነሽ በቀለ ከነተዘራ ሀ/ሚካኤል ከተፈራ ካሣ ከነእሳቱ ተሰማና የነበሩ ጊዜ ከነባር አርቲስቶች ሌሎችም በነበሩበት የሙዚቃ ቡድን ውስጥ በኦሮምኛ ነበር የምጫወተው፡፡

ባውዛ፡  አዳዲስ ትፈጥራለህ ወይስ ከተዘፈኑት ውስጥ ነው

መሀመመድ፡-  እኔ ከተዘፈኑት ዘፈኖች ውስጥ ነው፡፡ ከአሉት የሱዳንኛ ዜማዎች ጥሩ ጥሩ ዘፈኖችን ሳገኝ እዘፍናቸዋለሁ፡፡

ባውዛ፡-  ከሱዳንና ሱማልኛ ዘፋኞች ውስጥ የምታደንቃቸውና የምትወዳቸው እንድትዘፍናቸው ስሜት የሚሰጡህ እነማንን ነው፡፡

መሀመድ፡  ሱዳንኛና ሱማልኛ ዘፈን እዘፍናለሁ፡፡ የሱማልኛ ቋንቋ እሰማለሁ እንጂ ብዙም አልናገርም ዜማውንም በትክክል አዜማለሁ እኔ ሁሉንም አርቲስት ጥሩ ችሎታ ያላቸውን አደንቃለሁ፡፡ ከአገር ውስጥ ከማደንቃቸው እነ ጥላሁን ገሠሠን እነ መሀሙድ አህመድን እነ ይሁኔ በላይንም እነ ቴዴ አፍሮም እነ አስቴር አወቀንም — ከኦሮምኛ ዘፋኝ አንጋፋውን አንርቲስት አሊ ቢራን አደንቃለሁ ባጠቃላይ ጥሩ ሙያ ያላቸውን አደንቃለሁ፡፡

ባውዛ፡  ለማስታወስ ትችላለህ የመጀመሪያ ዘፈንህን

መሀሙድ፡  ለማስታወስ የመጀመሪያው ዘፈኔ ከውቢሻው ጋር አየተቀባበልን የምንዘፍነው ፋኢ ታኢ— በአማርኛ እባክሽን ከኔ አትራቂ የሚል ነበር፡፡ በቴሌቪዥንም ተቀርጾ ይታይ ነበር

ባውዛ  ወደ አዲስ አበበባ ከመጣህ በኋላ የት ትጫወት ነበር

መሀመድ፡  እንግዲህ ክቡር ዘበኛን ለቅቄ የወጣሁት በለውጡ ጊዜ ነው ከመጣሁ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ ዋዜማ አዳራሽ ማታ ማታ ከዚያም ደግሞ ዛምቤዚክ ይባል የነበር ማራቶን ሙኒክ ዜብራ ጊዬን ሆቴል ከኢትዬ ስታር ባንድ ጋርም እሠራ ነበር፡፡ ኢትዬ ስታር ከፈረሰ በኋላ ደግሞ ኤፍሬም እኔ ሆነን አበራ ተስፋዬ ደራመሩ ጊዩን ባንድ ተብሎ አንሠራ ነበር ከዚያ ከነ ዬሀንስ ተኮላ ጋር ዋሊያስ ባንድ ነፃነት መርህ አሌክሳንደር የሚባል ግርዬማ የሚባል ነበር፡፡ ሌላው ደግሞ ለአጭር ጊዜ አለማየሁ እሸቴ ባንድም ሸበሌ የሚባልም ነበር፡፡ ከነዚህ ሁሉ ጋር ቬኔስ ክለብ ድራም በመጫወትም እሰራ ነበር። ሌላው ደግሞ አሊ ቢራ ባንድ የሚባል ባንድ ለረጅም ጊዜ የነበረ አሊ ቢራ የነበረበት ነበር እሱ እንደወጣ ወደ ከአሊ ቢራ ባንድ ጋር እነ መራዊ ዩሐንስ ጋር አርብና ቅዳሜ ሸበሌ እጫወትና ሌላውን አምስቱን ቀን ደግሞ ካራማራ የባህል ምሽት ከባህሎች ጋር እሠራ ነበር፡፡

ባውዛ፡-  አሁን የምትኖረው አሜሪካን አገር ነው፡፡ መጀመሪያ ኢትዩጵያ እያለህ የውጭ እድል የገጠመህ ወደየት አገር ነበር፡፡

መሀመድ፡-  የመጀመሪያው የውጭ እድሌ ከኢትዩ ስታር ባንድ ጋር ዱባይና አቡዳቢ ሄደን ነበር፡፡ ለሁለት ወር ጊዜ ኮንትራት ይዘን ሰርተን ከተመለስን በኋላ ብዙም አልቆየሁም አንድ ፊንላንዳዊ ሚስት አግብቼ ኢንዶኔዥያ ውስጥ ብዙም የኢትዩጵያ ኮሚኒቲ ስላልነበረ አንድ እህቴ በጣም ታማብኝ በአስቸኳይ ወደ ሀገሬ ተመለስኩኝ

ባውዛ፡-  ወደ አሜሪካ መቼና እንዴት መጣህ?

መሀመድ፡-  ከኢንዶኔዥያ  አንደተመለስኩኝ  የመጀመሪያ  ካሴቴን  ሠርቼ  ጨርሼው  ለገበያ  የተለቀቀው ከተመለስኩ በኋላ ነበር፡፡ የአልበሙ ዝርዝር ኬኔ የሚለው የሶማልኛ ዘፈንና የተለያዩ ጥሩ ጥሩ ዘፊኖች የበሩበት ነበር፡፡ በጣም ቆንጆ ሁኔታ ላይ እያለ ወደ አሜሪካን ቪዛ ጠይቄ ተፈቀደልኝና ብዙም ዘፈኑ እንደወጣ ሳልቆይ እዚህ አገር መጣሁ፡፡ የመጀመሪያው ያረፍኩበት ሲያትል ዋሽንግተን ነበር፡፡ ከዚያም ከልጆቼ እናት ጋር ተገናኘሁ ከባለቤቴ ጋር ተጋባን፡፡

ባውዛ፡-  ልመጣልህ ነበር ወደ ቤተሰብህ አሁን ትዳር መስርተሀል ልጆች ወልደሀል

መሀመድ፡-  አዎ ባለቤቴ አሜሪካዊ ናት ተጋባንና 3 ልጆች ወልደን ለ7 ዓመት ከቆየን በኋላ ወደ ዋሽንግተን መጣን ከዚያም ሲያትልም ዋሽንግተንም እየተመላለሰን እንኖር ነበር በመጨረሻ ዋሽንግተን አልተሰማማትምና ወደ ሲያትል ተመለሰች ለጊዜው ተለያይተናል አሁን እሷ ከልጆቼ ጋር አብራ እዚያ ትኖራለች፡፡ አሁን ተፋተናል፡፡ ከተለያየን 8 ዓመት ሆኖናል፡፡

ባውዛ፡-  ልጆችህ ማን ማን ይባላሉ

መሀመድ፡  የመጀመሪያ ልጄ ናዲያ መሀመድ ትባላለች የ15 ዓመት ልጅ ነች ሁለተኛዋ ልጄ ደግሞ የእናቴን ስም ነው የሰጠኋት መዲና መሀመድ ትባላለች ወንዱ ልጄ 12 ዓመቱ ነው አሚር መሀመድ ይባላል፡፡ ከመጀመሪያዋ ሚስቴ ከተለያየሁ በኋላ ግን በአሁኑ ሰዓት ሁለተኛዋ ሚስቴ ከጅማ የምትወለድ ስትሆን ሙኒራ አባቢያ ትባላለች ከሷ ጋር መኖር ከጀመርኩ አሁን ወደ አምስት ዓመት ጨርሰን 6ኛ ዓመታችንን ይዘናል፡፡

ባውዛ፡  መሀመድ የመድረክ ላይ እንቅስቃሴህን በጣም ማራኪ መሆኑን ብዙ ሰዎች ያደንቁሀል ይወዱሀል በውጪ ሲያዩህ ደግሞ እርጋታ የተሞላበት ባህሪ ነው የሚታይብህ የመድረኩ ሚስጥር ምንድን ነው

መሀመድ፡  የሙዚቃ ፍቅር ነው ያለኝ የሙዚቃ ስሜት ነው ሌላ ከሙዚቃ ውጭ ሊያንቀሳቅሰኝ የሚችል ነገር የለም፡፡ የኔ ሞተር የኔ አንቀሳቃሽ የሙዚቃ ፍቅር ነው እና ጥሩ ሙዚቃ ጥሩ ዜማ በምሰራበት ጊዜ ሳይታወቀኝ የመድረክ እንቅስቃሴየን ያጉላዋል፡፡ ባጠቃላይ የሙዚቃና የህዝብ ፍቅር ነው ብዬ ልነግርህ እወዳለሁ፡፡

ባውዛ፡  ወደ አገር ቤትስ ሄደህ ታውቃለህ ምን እያሰብክ ነው

መሀመድ፡  አገር  ቤት  ሄጃለሁ  ለአንዳንድ  ጐዳዮችም  ቤተሰብን  ለመጠየቅም  እሄዳለሁ  እኔ  በጠቅላላ አነጋገር ዛሬ ነገ ምን አለኝ ምን ይዥ ሞላልኝ አልሞላልኝ ስል ሬሣዬ በመጨረሻ በሳጥን ተጭኖ እንዲሄድ አልፈልግም፡፡ አሁን በህይወቴ እያለሁ የሰው ፍቅር እያለኝ አቅም እያለኝ መሄድ መንቀሳቀስ መዝለል በምችልበት እድሜ ላይ እያለሁ እግዚአብሄር  ከፈቀደልኝ  መሄድ  እፈልጋለሁ፡፡  እና  ሀገሬ  ላይ  ከሚወደኝ  ህዝብ  ማገልገል  የምፈልገው  ጊዜ  ኖሮኝ ፈጠራዎቼንም በብዛት ለመስራት አገር ላይ እንደሚመች እዚህ አገር አይመችም ስለዚህ ከምንም ነገር በላይ ወደ አገሬ አርጅቼ  በዱላ ወይም ሞቼ በሳጥን ከመሄዴ በፊት አሁን ወደ አገሬ ለመሄድ ተነሳስቻለሁ፡፡

ባውዛ፡  ጠቅልለህ መግባት ነው ወይስ

መሀመድ፡  ልጆቼ እስካሉ ድረስ ትምህርታቸውን እስኪጨርሱ ድረስ እየተመላለስኩ አያቸዋለሁ በተረፈ ግን አገሬ ላይ ከዚህ የተሻለ እንቅስቃሴ የሙዚቃ ህይወቴን የማሻሽልበት በሀገሬ ስለሆነ የሙዚቃ ፍቅር ነው የሚያቆራኘን በሁሉም ነገር ጥሩ ካሳለፍኩት የበለጠ በሀገሬ ውስጥ የሙዚቃ እድገት እንደማመጣ ሙሉ እምነት አለኝ፡፡

ባውዛ፡  የኢትዩጵያን ሙዚቃ በአሜሪካ እንዴት ታየዋለህ ለወደፊትስ ሊደርስ ይችላል ብለህ የምትገምተው ሀሣብ ካለ ምንስ ብናደርግ የሀገራችን ሙዚቃ ሊያድግ ይችላል ትላለህ

መሀመድ፡  ሙዚቃችን  እንዲያድግ  እዚህ  ያለውን  ጥሩ  ነገር  በመውሰድ  ያለማቋረጥ  ከሞከርን  እድገት ይመጣል ግን ምን ጊዜም ቢሆን እንደ አገር የለም፡፡ በእርግጥ ሙዚቃ ለመማር ቢሆን ከሀገራችን የበለጠ ቴክኖሎጅው ሰፋ ያለ ስለሆነ የበለጠ ያንን ለመማር ጊዜ ኖሮት የቻለ ጥሩ ነው በተረፈ ግን ለፈጠራ የጊዜ ብቃት በሀገራችን እናገኛለን፡፡ እዚህ ያ የጊዜ ብቃት የለም ስለዚህ ባለበት መሄድ ነው የሚሆነው

ባውዛ፡  ብዙ ሰው ሲያይህ በቁመትህና በፀጉርህ ምክንያት የሌላ አገር ዜጋ ይመስላል ሲሉ ይሰማል ረጅም ፀጉርህን እንዴት አሳደግኸው ከስንት ዓመትህ ጀምሮ ነው የፀጉርህ እድገቱ

መሀመድ፡  ፀጉሬን  ማሳደግ  የጀመርኩት  ገና  የመጀመሪያውን  ካሴቴን  እየሰራሁ  እያለሁ  ነው፡፡  ፀጉሬን የማሳድገው ምንም ማንንም አይቼ አይደለም ማሳደግ የጀመርኩት የራሴ ፍላጐት ስለነበር ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ወደ ፀጉር ቤት ለመስተካከል ስሄድ አንድም ቀን ተደስቼ አላውቅም፡፡ ምክንያቱም ፀጉሬ ለማስተካከል የማያመች ስለ ሆነ ለፀጉር አስተካካዬቹ  አይመቻቸውምና  ነው፡፡  ስለዚህ  በዚህ  ምክንያት  ተውኩት  መቆረጡንና  እንደ  ድሬድ  ሆኖ  ቀረ  በ1989 በፈረንጅ 19ኛ ዓመት አካባቢ ነው ለዛውም በየ ዓመቱ ትንሽ ትንሽ ይቆረጣል ያለዚያማ መሬት ይጐተት ነበር፡፡

ባውዛ፡  እስቲ ወደ አርቱ ልመለስና የምታደንቀው አርቲስት ማን ነው ለሙዚቃዬ መነሻ ነው የምትለው ካለ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር ዘፋኞች

Mohamed Tewil (Bawza Photo)

መሀመድ፡  ከውጭ አገሮቹ እንደ የኑስ አብድላሂ አብዱላሄ የሶማሊኛ ዘፋኞች ስሰማ በጣም እደሰት ነበር፡፡ አል ቢራንም በኋላ በኋላ ስሰማው አስገራሚ ድምጽና ችሎታ አለው ሌላ እነ ጥላሁንን እነ መሀሙድን አንጋፋዎችን ከውጭ ደግሞ እነ መሀመድ ወርዲን በጣም አደንቃለሁ አሁን ከመጡ ደግሞ በጣም እሣት የሆኑ ልጆች አሉ በጣም አደንቃቸዋለሁ፡፡

ባውዛ:  በቅርብ ያወጣኸው አዲስ አልበም በየቦታው እየተደመጠ ነው ይህን ሙዚቃውን ማን ሠራልህ ስንት ጊዜ ፈጀብህ

መሀመድ:  ከዚህ በፊት 2ኛ አልበሜን ያወጣሁት ሲሲ የሚባል ከአበጋዝ ክብረወርቅ ጋር የሰራሁት የተለያዩ የተለመዱ ዘፋኖችን ያካተተ ካሴት ነበር፡፡ እሱ በጣም ቆንጆ ነበር፡፡ አሁን እንግዲህ አስር ዓመት ምን ልስራ እያልኩ ያሰብኩበት እዚህ ከመጣሁ ብዙ ጊዜ ወስጃለሁ ሥራውን ለመስራት በተለያዩ ምክንያቶች ያልተመቻቹልኝ በመሆናቸው ነበር፡፡  ከብዙ  ጊዜ  በኋላ  ከዚህም  ከዚያም  ብዬ  የተለያዩ  ደራሲዎች  የተሳተፉበትን  ዘፈን  በጣም  ከታዋቂው  ኪቦርድ ተጫዎች ጋር ጀመርኩኝ መጀመሪያ ለመስራት ያሰብኩት ከአበጋዝ ጋር ነበር እሱም ወደ አገር ቤት ሄደ እሱ እዛ እኔ እዚ ሆኖ መስራት አዳጋች በመሆኑ ከብርሀኔ ጋር ጀመርኩኝ ታዋቂውን ሳክስፎኒሰት ሞገሱን በሊድ ጊታር ደግሞ የድሮው የሮሀ ባንዱ ሊድ ጊታሪስትን በማካተት እንደሁም የኔሰው ተፈራን በቤዝ ጊታርነት በማድረግ ይህንን የመሰለ ሥራ ለመስራት ችየለሁ፡፡

ባውዛ፡-  ድርሰቶቹ በብዛት ያንተ ናቸው

መሀመድ፡-  ብዙዎቹን ዘፈኖች የተለያዩ ገጣሚዎች ናቸው የፃፉት ዜማዎቹ በብዛት የኔ ናቸው፡፡ ኮምፖዝ ያደረግሁትም እኔ ነኝ

ባውዛ፡-ለአድናቂዎችህ በዚህ አጋጣሚ የምታስተላልፈው መልዕክት ካለ

መሀመድ፡-  መቼም የፈለገውን ያህል ተለፍቶ ቢሠራ ህዝብ ካላደነቀው እውነት ለመናገር ለብቻዬ ምንም አያስደስተኝም ሥራዬን ሰምተው የወደዱልኝን ኢትዩጵያውያንንም ሆነ በውጭው አለም ያሉትን አድናቂዎቼን ከልብ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባለሁ ሁሉንም አድማጮቼን በሙሉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ

ባውዛ፡  እሽ መሀመድ እኛ የባውዛ ጋዜጣ አዘጋጆች ለቃለ ምልልሳችን ፈቃደኛ በመሆንህ ከለብ ልናመሰግንህ እንወዳለን መልካም ጊዜ

መሀመድ:   እኔም የባውዛን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል እድሉን ስለሰጣችሁኝ በጣም አመሰግናለሁ፡፡

Here is the new interview with Seifu on EBS

መሀመድ ጠዊል

አንጋፋው ድምፃዊ መሀመድ ጠዊል ዘፈን አቆመ። በተጨማሪም ፀጉሩን እና የድሮ ካሴቶቹን ማቃጠሉን አሳወቀ።

Posted by Bawza Ethiopian Newspaper on Monday, April 30, 2018

 

The post Oromo music legend Artist Mohammed Tewil quiet music appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles