Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

U.S. military veteran receives world’s first total penis and scrotum transplant

$
0
0

A U.S. serviceman extremely harmed quite a while back in an IED blast in Afghanistan has gotten the world’s first total penis and scrotum transplant, specialists at the Johns Hopkins University School of Medicine declared Monday. Here is the Amharic version of the news:

ንቅለ-ተከላውም የተከናወነው የወንድ ብልትና የመራቢያ አካላት እንዲሁም የሆድ አካባቢ ህዋሳትን ከሞተ ለጋሽ በመውሰድ ነው። ከአስራ አራት ሰዓት በላይ በወሰደው በዚህ ንቅለ-ተከላ ላይ አስራ አንድ ዶክተሮች ተሳትፈውበታል። በጦርነት ላይ ለተጎዳ ወታደር ሲከናወን የመጀመሪያው የሆነው ይህ ንቅለ-ተከላ፤ ከዚህም በተጨማሪ ከሆድ አካባቢ፣ ሙሉ በሙሉ የወንድ መራቢያ አካላትንና ህዋሳትን በመውሰዱ ፈር ቀዳጅ ነው ተብሏል። ዶክተሮቹ ጨምረውም ቆለጡ ሞራላዊ በሆነ ምክንያት ንቅለ-ተከላ መደረግ እንዳልተቻለም ተገልጿል። የሞተው ለጋሽ ማንነትም እንዲሁም የሞቱ ምክንያት አልተገለጠም። የለጋሹ ቤተሰቦች ወታደሩን ላገሩ ላበረከተው አስተዋፆ አምስግነው ለጋሹ ባደረገው ለገሳ እንደሚኮራ ገልፀዋል(“We are so thankful to say that our loved one would be proud and honored to know he provided such a special gift to you,”.
በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የፕላስቲክና መልሶ ጥገና ኃላፊ የሆኑት ዶክተር አንድሪው ሊ እንዳሉት “ፊት ለፊት የሚታዩ የተቆረጡ አካላት ጉዳታቸውም ይታያል፤ አንዳንድ የጦር ጉዳቶች ግን የተደበቁ በመሆናቸው ተፅኗቸውም በብዙዎች አይታዩም” ብለዋል። በመራቢያ አካላት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችንም “የጦርነት ያልተነገረላቸው ጉዳቶች” ብለዋቸዋል።                                                      በአውሮፓውያኑ 2014 በጆንስ ሆፕኪንስ አስተባባሪነት “ግንኙነት ከጉዳት በኋላ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሲምፖዚየም “ከባለቤቶቻቸው፣ ከቤተሰቦቻቸውና ከሚንከባከባከቧቸው ግለሰሰቦች እንደሰማነው፤ በብልታቸው አካባቢ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች በማንነታቸው ላይ፣ በራሳቸው ላይ ያላቸው እምነት እንዲሁም በግንኙነታቸው ላይ ከፍተኛ ማሽቆልቆል ያጋጥማቸዋል” ብለዋል። ስሙ እንዳይገለፅ የፈለገው ወታደርም ለዩኒቨርሲቲው እንደተናገረው “ዛሬ ከእንቅልፌ ስነቃ እንከን የሌለኝ መስሎ ተሰማኝ፤ በመጨረሻም ደህና ሆንኩኝ” ብሏል። ይህ ወታደር ጉዳቱም የደረሰበት አፍጋኒስታን ውስጥ በሚራመድበት ወቅት የተደበቀ ቦምብ እረግጦ ነው።

ይህ ንቅለ-ተከላ ቆዳ፣ አጥንት፣ ጡንቻዎችን እንዲሁም የደም ስሮችን ሁሉ ያካተተ ሲሆን የቀዶ ጥገና ባለሙያዎቹም ግለሰቡ ከ6-12 ወራት ሙሉ በሙሉ እንደሚያገግም ገልፀዋል። የንቅለ-ተከላው ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ሪክ ሬዴት በበኩላቸው ወታደሩ እያገገመ መሆኑንና በቅርቡም ከሆስፒታል እንደሚወጣ ተናግረዋል። “ንቅለ-ተከላው ሽንቱን በትክክል እንዲሸና እንዲሁም ሌሎች ግንኙነቶችን እንደሚያሻሽልለትና ጤናማ ህይወት ሊኖረው እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን” በማለት የሚናገሩት ዶክተሩ ለወደፊትም ለሌሎች ጉዳተኞች ተመሳሳይ የሆነ ንቅለ-ተከላ ሊያካሂዱ እቅድ እንደያዙ ተናግረዋል። የንቅለ-ተከላው ቡደን በበኩሉ የኒቨርስቲው 60 የሚሆኑ የመራቢያ አካላት ንቅለ-ተከላ እቅድ እንደያዘም ተግረዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው የእስኪት ንቅለ-ተከላ የተደረገው በደቡብ አፍሪካ የቀዶ ጥገና ባለሙያዎች በአውሮፓውያኑ 2014 ነው።
Source: BBC and usatoday

 

The post U.S. military veteran receives world’s first total penis and scrotum transplant appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles