ድምፃዊ ታምራት ደስታ ዛሬ በድንገት ሕይወቱ ማለፉ ተነገረ፡፡ ድምፃዊው ህመም ተሰምቶት መኪና እየነዳ ወደ ስላሴ ክሊኒክ ሲሄድ ድንገት ራሱን መሳቱንና በኋላም በአምቡላንስ ወደ ምኒልክ ሆስፒታል ተወስዶ ህይወቱ ማለፉ መረጋገጡን ሸገር ራዲዮ በፈስቡክ ገፁ አስነበቧል።
ድምፃዊ ታምራት ደስታ ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር፡፡
ባውዛ ለቤተሰቡና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
The post Breaking News: Artist Tamerat Desta Passed away appeared first on Bawza NewsPaper.