መራኄ መንግሥት አብይ አሕመድ በጠቅላይ ሚኒስትነት የመጀመሪያ የሥራ ጉብኝታቸውን ዛሬ፣ ቅዳሜ መጋቢት 20/2010 ዓ.ም. ሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጂጂጋ ላይ አድርገው ውለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው የፌደራሉ መንግሥት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ተልዕኮ በኦሮምያና በሶማሌ ክልሎች አዋሣኝ ወረዳዎች ላይ ለተከሰቱ ግጭቶችና ለተከተለውም ቀውስ ዘላቂ መፍትኄ ማስገኘት እንደሆነ ተገልጿል።
በሁለቱ ክልሎች መካከል ለብዙ ሕይወት መጥፋትና ቁጥራቸው እጅግ ለበዛ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት የሆኑት ችግሮች ከተጫሩ አንስቶ የሃገሪቱ መሪ ወደ አካባቢዎቹ ሄዶ አያውቅም።
ጂጂጋ ከተማ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለመንግሥቱ ልዑካን የተደረገው አቀባበል የሞቀ እንደነበር አንድ የጂጂጋ ዩኒቨርሲቲ መምህር ለቪኦኤ ተናግረዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
The post Official visit of PM Dr. Abiy Ahmed to Ethio-somali region(Jigjiga) of Ethiopia: VOA appeared first on Bawza NewsPaper.