በኢትዮጵያ ታሪክ በክብደቱ ሁለተኛ የሆነ የማህጸን እጢ በቀዶ ህክምና ማውጣት መቻሉን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የሕክምና ኮሌጅ አስታወቀ።
44 ኪሎ ግራም የሚመዝነው እጢ በቀዶ ህክምና የተወገደላቸው ወይዘሮ ንጋቷ ወልደማርያም በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።
ከዘጠኝ ዓመት በፊት ከእግራቸው በጀመረው ህመም ምክንያት ራሳቸውን መርዳት አቅም ስላሳጣቸው ባለፉት ሶሰት ዓመታት ቤተክርስቲያን ደጅ በምዕመናን እየተረዱ እንደቆዩ ነው የተነገረው።
ህመሙ እየተባባሰባቸው መናገርና መራመድ እያቃታቸው ሲሄድ ሰዎች ወደ ህክምና ተቋም በምጣታቸው ህክምናውን ማግኘት እንደቻሉ ተናግረዋል።
በሆስፒታሉ የማህጸንና ጽንስ ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ቤተል ደረጄ እንደተናገሩት፥ በአገሪቷ በክብደቱ ሁለተኛ በቅዱስ ጳውሎሰ ሆስፒታል ታሪክ ደግሞ የመጀመሪያ የሆነ የማህጸን ዕጢ ቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።
በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነና 64 ኪሎ ግራም ክብደት ያለው የማህጸን እጢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በቀዶ ህክምና መውጣቱ ይታወሳል።
ምንጭ፦ ኢዜአ
The post Ethiopia: Forty-four Kilo gram of uterine fibroids (tumor) surgically removed at St. Paul’s Hospital appeared first on Bawza NewsPaper.