በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ ትናንት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ38 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።
አደጋው ከመካነ ሰላም ተነስቶ ወደ ደሴ 48 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተሽከርካሪ ላይ ነው የደረሰው።
የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሱ በለጋምቦ ወረዳ ከገነቴ ከተማ በቅርብ ርቀት አቧራ ጥግ የሚባለውን ጠመዝማዛ መንገድ እንደጨረሰ መንገዱን ስቶ በመውደቁ ነው አደጋው የደረሰው።
በትናፊክ አደጋውም 28 ወንድና 10 ሴት በድምሩ የ38 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ 10 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት አደጋ ደርሶባቸዋል ብለዋል።
በአደጋው ጉዳይ የደረሰባቸው አብዛኞቹም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች መሆናቸውነም የለጋምቦ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቀቋል።
በአሁኑ ወቅትም ጉዳት የደረሰባቸውን ተሳፋሪዎች በአቀስታ ከተማ ህዳር 11 ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የገለፀው ጽህፈት ቤቱ፥ ጉዳታቸው ከሆስፒታሉ አቅም በላይ የሆኑት ደግሞ ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል መወሰዳቸውን ገልጿል።
Source: Fanabc.com
The post At least 38 people killed in a bus crash in Legambo Woreda, South Wollo zone, Ethiopia appeared first on Bawza NewsPaper.