Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Astrology and Fortune-telling, a $3.7bn business in South korea

$
0
0

DESTINY is typically said to sneak in substantial window hangings of purple velvet, in the devilish gleam of a precious stone ball, behind a cloak of overwhelming incense or in the tuck of a gold-chiffon turban. Here is a short history translated in to amharic about Astrology and fortune-telling in South Korea

በደቡብ ኮርያ በኮከብ ቆጠራና በጥንቆላ ተግባር ላይ የተሰማሩና የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ እንደሚገኝ ያስነበበው ዘኢኮኖሚክስ፤ ከአጉል ልማዶቹ ጋር በተያያዘ በየአመቱ የሚንቀሳቀሰው አጠቃላይ ገንዘብ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ 3.7 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክቷል፡፡

በደቡብ ኮርያ በየአደባባዩና በየቤቱ ጧት ማታ፣ የኮከብ ቆጠራና የጥንቆላ ተግባር የሚያከናውኑ ሰዎች እየተበራከቱ ነው ያለው ኒውስዊክ፤ የኮርያ ነቢያት ማህበርም በአገሪቱ ከ300 ሺ በላይ ኮከብ ቆጣሪዎችና 150 ሺ ገደማ ጠንቋዮች እንዳሉ መገመቱን ጠቅሷል፡፡ በመጫወቻ ካርዶች የሚከናወኑ የኮከብ ቆጠራና የእለት ዕጣ ፋንታ ትንቢቶች፣ በአገሪቱ ለረጅም አመታት የተለመዱ ድርጊቶች እንደሆኑ ያስታወሰው ዘገባው፤ አሁን አሁን ደግሞ በቴክኖሎጂ የታገዙ የሞባይል አፕሊኬሽን ጥንቆላዎችና ኮከብ ቆጠራዎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ገልጧል፡፡

ሃንዳሶፍት የተሰኘው ታዋቂ የአገሪቱ ሶፍትዌር አምራች ኩባንያ፣ ባለፉት አምስት አመታት ብቻ 13 ያህል የጥንቆላና የዕለት ውሎ ትንበያ ሶፍትዌሮችን አምርቶ በገበያ ላይ ማዋሉን ያስታወሰው ዘገባው፤ ጂኦምሲን የተባለውና ከ2 አመታት በፊት ገበያ ላይ የዋለው ተወዳጅ የውሎ ትንበያ የሞባይል አፕሊኬሽን ሶፍትዌር፣ከ3 ሚሊዮን ጊዜ በላይ ዳውንሎድ መደረጉን አውስቷል፡፡
ኮርያ ኢኮኖሚክ ደይሊ የተባለው የአገሪቱ ጋዜጣ ባለፈው አመት ያወጣው መረጃ በበኩሉ፤የአገሪቱ ዜጎች በማህበር ተደራጅተው ኮከብ በማስቆጠርና በማስጠንቆል፣ ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን በከንቱ በማባከን ላይ እንደሚገኙ ጠቁሞ፣ ኮርያን ኪዩንግሲን ፌዴሬሽንና የጥንቆላ ማህበር የተባሉት ሁለት የአገሪቱ ታዋቂ ማህበራት ብቻ በድምሩ አንድ ሚሊዮን ያህል አባላት እንዳሏቸው አመልክቷል፡፡ በማህበር የታቀፉ አስጠንቋዮች ቁጥር ባለፉት አስር ዓመታት በእጥፍ ማደጉንም ጋዜጣው አክሎ ገልጧል፡፡

Source: The Economist and addis admass newsletter

 

The post Astrology and Fortune-telling, a $3.7bn business in South korea appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles