Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Meet 256-Year World’s Oldest Man With 200 Chidren – Li Ching-Yuen

$
0
0

Li Ching-Yuen was a Chinese herbalist, martial artist and tactical advisor, known for his supposed extreme longevity.

“ለመሆኑ ሃሳባችን የህመማችንም የፈውሳችንም ምክንያቶች እንደሆኑ ታውቃላችሁ!?”
★ ★ ★ ★ ★

……..በጥንቱ የእምነት መፅሓፍ ላይ ረጅም ዕድሜ ስለኖሩ ሰዎች ስናነሳ በድንገት የሚመጣልን የዕድሜ ባለፀጋ መቼም ለአንድ ሺ አመት ጎረቤት ሆኖ ያረፈው “ማቱሳላህ” መሆኑ አይቀርም። ይሄ ሩቅ ጊዜ ይመስለኛል!! ሆኖም በዓለማችን ላይ አስገራሚ ገድል ከሰሩ ሰዎች ውስጥ ታዲያ ” በNEW YORK TIMES ” ጋዜጣ ከፍተኛ ሽፋን የተሰጠውና በራሱ በቻይና መንግስት ማረጋገጫ የተሰጣቸው “ሊቼንግ ዩኤን” ናቸው። እኚህ ሰው በሕይወት ዘመናቸው ከ23 ሚስቶች ጋር አንሶላ በመጋፈፍ 200 ልጆችን ያፈሩ ዕድሜ ጠገብ አዛውንት ናቸው።
……ስለሰውዬው እንደተዘገበው ከሆነ እኚህ ተዓምራዊ የቻይና ዜጋ የተወለዱትና ምድርን የተቀላቀሉት እ,ኤ,አ በ1636 ዓመተ ምህረት ሲሆን፣ ዕድሜ ዘመናቸውን ሁሉ ያሳለፉት የተለያዩ መድሃኒቶችን ሲፈጥሩና ጎን ለጎን የጦር ጥበቦችን ሲለማመዱ ነበር።
የ1930 የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዘገባ ስለሰውዬው በስፋት ሃትቶ የወጣው በቻይና መንግስት የተቀመጠን ማስረጃ ይፋ አድርጎ ነበር። የማስረጃው አንኳር ነጥብ ሆኖ የቀረበው የአዛውንቱን የሊቺንግ ዩኤን 150ኛ አመት የልደት በዓልን የተመለከተውን ” የእንኳን ደስ አልዎት” የምስክር ወረቀትን ነበር።
ለመሆኑ እኚህ ቻይናዊ አዛውንት ይሄን ያህል አመት ዕድሜ እንዴት በሕይወት ሊቆዩ ቻሉ? ለሚለው ሊቺንግ ይሄን ያህል የዕድሜ በረከት ያዘነበላቸውን ምክንያት ሲጠየቁ በአንድ መስመር ……..” የራሴ ልብ ባለቤት መሆኔ፣ እንደኤሊ መቀመጤ፣ እንደውሻ መተኛቴና ስራመድ ፈጣን መሆኔ” ሲሉ ይገልፁታል።
…….የራስ ልብ ባለቤት መሆኔ ማለታቸው የፍቅርና ክብካቤ ሰው መሆናቸው፣ እንደኤሊ መቀመጤ ማለታቸው በቀን ውስጥ ተመስጧዊ ሜዲቴሽን በማድረግ ማሳለፋቸው፣ እንደውሻ መተኛቴ ማለታቸው ዘና ያለ ዕረፍትን ማድረጋቸውና ሲያወሩና ሲራመዱ ደግሞ ፈጣን መሆናቸውን ያብራራሉ።
…….በአንድ ወቅት የቻይና ጦር ጄኔራል የነበሩት “ያንግሌን” አዛውንቱን ወደጦር ካምፓቸው በማምጣት እንዲጎበኙ ጋብዘዋቸው ነበር። ለቻይና ወታደሮችም የጦርነት ጥበባቸውንና ልምዳቸውንም እንዲያካፍሉም ጠይቀዋቸው ነበር። የሚገርመው በወቅቱ አዛውንቱ 250ኛ ዕድሜያቸው ላይ ቢሆኑም በጣም በንቃት ጄኔራሉን የሚያስደምሙ ወታደራዊ ስልጠናዎችን ነበር ለመስጠት የቻሉት።
…….ሊቺንግ ዩኤን በሞት የተለዩት እ,ኤ,አ ግንቦት 6/1933 ሲሆን፣ በመጨረሻዋ ሰአት በሕይወት ዘመናቸው ማከናወን የነበረባቸውን ብዙዎቹን ተግባራት ስለመፈፀማቸውና ወደዘላለማዊ ቤታቸው የመሄጃቸው ትክክለኛዋ ሰዓት መድረሱን ነበር ለወዳጆቻቸው የተናገሩት።
……መቼም ከ100 አመት በላይ ስለሚኖሩት ስለሰሜኖቹ የዓለማችን ሕዝቦች የጤና ሚስጥርና ስለምስራቆቹ የዩጋ ጠበብቶች ታሪክ ማግኘት አይከብድም። እነዚህ ሰዎች ረጅም ዕድሜ ብቻ አይደለም የቆዩት…..ተፈላጊነትን፣ ንቁነትንና ትጋትን ጭምር ማዳበር የቻሉ ናቸው እንጂ። እናም “ከእነሱ ምን ልንማር እንችላለን!?” ነው መሰረታዊው ጥያቄ።
…….በአሉታዊ አመለካከትና በስሜት መጨናነቅ ሳቢያ የሚመጡ በሽታዎች ” Psychosomatic” በመባል ነው የሚጠሩት። እነዚህም ለጤና አጠባበቅ ሥርዓቱ ራስ–ምታት መሆናቸው አልቀረም። ሐኪሞችና ተመራማሪዎች በአንድ ድምጽ…..አመለካከታችን በቀጥታ የውስጥ አካላችንና የሰውነታችን አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ተፅህኖ ሊያሳድር እንደሚችል ይስማማሉ።
……..ጥንታዊ ህክምናዎችም ከሰውነት ባለፈ አዕምሮንም የማከም አቅም እንደነበራቸው ይታመንባቸዋል። ዘመናዊ ሕክምና በሌላ መልኩ በበሽታዎች ውጤትና በሰውነት ላይ በሚያስከትለው ሕመም ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰራ ሆኗል፣ ለዚህም ነው ብዙ ጊዜ በሽታዎች በሰው ላይ ደጋግመው የሚከሰቱት።
…….ለጤናችን ትልቁ ሚስጥር የሚገለጠው እዚህ ጋር ነው፣ አመለካከታችን ከበሽታችን ሊፈውሰን ወይም ሊያብስብን ይችላል። በበርካታ አጋጣሚዎች በሃሳባቸው ብቻ ከበሽታቸው የተፈወሱ ሰዎችን ተሞክሮ ሰምተናል። አንዳንዶቹ ኽንዳውም በዶክተሮችና በህክምና ጠቢባን ሳይቀር ምንም ተስፋ እንደሌላቸው የተነገራቸው እንደነበር ተገልጿል።
…….ከእነዚህ ታሪኮች መካከል አንዱ የሞሪሰን–ጉድማን ታሪክ ይገኝበታል። እ,ኤ,አ በ1981 ዓመተ ምህረት በአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ምክንያት በሆድና በሳምባው ጡንቻ ላይ በደረሰበት መቀደድ እንዲሁም በአከርካሪው ስብራት ሳቢያ እንደሚሞት በህክምናው መስፈርት በትክክል የታመነበት ሰው ነበር። መጀመሪያ መቆየት የቻለው በሰው–ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ ነበር። በወቅቱም ማድረግ የሚችለው ዓይኑን ማርገብገብ ብቻ ነበር። አደጋው እንደዚህ የከፋ ቢሆንም ሞሪሰን ግን በሓሳብ ኃይል ያምን ነበር። ጥቂት የሚባሉ ቀናትም በራሱ ኃይል በሆድና በሳንባው መካከል የተጎዳውን ጡንቻ መተካት ሲችል፣ ያለማንም አጋዥ መተንፈስ ችሎም ነበር። ጥቂት ቆይቶም ተሠብሮ የነበረውን አከርካሪውን በማገገም እግርና እጆቹን በራሱ ወደማንቀሳቀስ ደረጃ ተሸጋገረ። ዶክተሮቹ ግን አጠገባቸው ምን እየተከናወነ እንደሆነ እንኳ መረጃው አልነበራቸውም። ምክንያቱም ከዚህ በፊት መሰል ሁኔታ ገጥሟቸው አያውቅምና ነው። ከጥቂት ወራት በኋላ ሞሪሰን–ጉድማን መራመድ ጀመረ፣ ሙሉ በሙሉም ከአደጋው አገገመ። ይሄ እንግዲህ ከብዙ ታሪኮች መካከል የሚመዘዝና በእውን የተከሰተ ነው። ይህ ታሪክ ሓሳባችን የማይድኑ በሽታዎችን የመፈወስ አቅም እንዳለው ጥሩ ማሳያ ሆኗል። የጥንታዊው “የአዩርቬዲክ” የጤና ሣይንስ፣ ሳይኮሶማቲክ በሽታ ስለመኖሩ ብቻ አይደለም ማረጋገጫ የሰጠው!! ይልቁንም በልዩ የሰዎች ባህሪያት ስለሚከሰቱ አንዳንድ በሽታዎች ጭምር እንጂ። ለእናንተ የሰው ዕድሜ የሚያሳጥሩ አካላዊ ኢንፌክሽኖች እና ህመሞች ብቻ ይመስላችኋል አይደለም? አትሳሳቱ እነዚህን በተለይ አሁን በምንኖርበት ዘመን የሚያጠቁንና የማይታዩ በሽታዎች ተሸክመን እየኖርን ነውና ከላያችን እናራግፋቸው። ለመፈወስ ቢከብዷችሁ እንኳን በጥቂቱ እወቋቸው……

★ “ቅናት”…….የኢሚዩን ሥርዓትን ለሚያዳክመው የኦንኮሎጂካል በሽታ አሳልፎ ያስረክበናል።

★ “ቂም” ……ለእንቅልፍ ማጣትና ለጉሮሮ በሽታ ምክንያት ይሆናል።

★ “ለነገሮች መፍትሔ መስጠት ያለመቻል”……ይሄም ለሳንባ በሽታ አይነተኛ ድርሻ አለው።

★ “ውሸት”…..ለመጠጥ ሱሰኝነትና በሽታን የመቋቋም ችግር ያስከትላል።

★ “ጠብ–አጫሪነት”……ለሆድ ቁስለትና ለከፋ የኪንታሮት ደዌ ያጋልጣል።

★ “ዝምተኝነት”…..ለመዘንጋትና ለኩላሊት በሽታ አሳልፎ ይሰጣል።

★ “ጭካኔ” ……ለሚጥል በሽታ፣ ለአስምና ለደም–ማነስ በሽታ እንካችሁ ይለናል።

★ “ጠበኛነት”…..ከልክ ላለፈ የዕጢ ዕድገት ምክንያት ይሆናል።

★ ” በቃል ያለመርጋት ወይም ከሃዲነት”…..መካንነትን ያመጣል።

★ ” ባለጌነት”…..ለስኳር ህመምና ለልብ ህመም ዌይተር ሆኖ ያገለግላል

ከ Temesgen Badiso Facebook የተወሰደ

The post Meet 256-Year World’s Oldest Man With 200 Chidren – Li Ching-Yuen appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles